ጢሮስ ሰባ ዓመት ያኽል ተረስታ የምትኖርበት ጊዜ ይመጣል፤ ይህም የአንድ ንጉሥ ዕድሜ ነው፤ እነዚያ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ጢሮስ እንደ ዘማዊት ሴት እንዲህ ተብሎ ቅኔ የሚነገርባት ትሆናለች፦
ኢሳይያስ 23:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ የተረሳሽ ዘማዊት በገናሽን እየደረደርሽ በከተማ ውስጥ ዙሪ! እንዲያስታውሱሽ ጣዕመ ዜማ አሰሚ፤ ብዙ መዝሙሮችንም ዘምሪ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንች የተረሳሽ ጋለሞታ፤ በገና አንሺ፤ በከተማዪቱ ውስጥ ዙሪ፤ እንድትታወሺም፣ በገናሽን አሳምረሽ ምቺ፤ ብዙ ዘፈን ዝፈኚ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፥ መሰንቆ ያዢ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ ዘፈንሽንም አብዢ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፥ መሰንቆ ያዢ፤ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ፤ ዘፈንሽንም አብዢ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፥ መሰንቆ ያዢ በከተማ ላይም ዙሪ፥ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ ዘፈንሽንም አብዢ። |
ጢሮስ ሰባ ዓመት ያኽል ተረስታ የምትኖርበት ጊዜ ይመጣል፤ ይህም የአንድ ንጉሥ ዕድሜ ነው፤ እነዚያ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ጢሮስ እንደ ዘማዊት ሴት እንዲህ ተብሎ ቅኔ የሚነገርባት ትሆናለች፦
ከሰባ ዓመት በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞ የንግድ ሥራዋ እንድትመለስ ያደርጋታል፤ በምድር ላይ ከሚገኙ መንግሥታት ሁሉ ጋር ታመነዝራለች።
ወዳጆቻችሁ ሁሉ ረስተዋችኋል፤ እነርሱ እናንተን አይፈልጉአችሁም፤ ኃጢአታችሁ የበዛ፥ ክፋታችሁም እጅግ ከፍ ያለ ስለ ሆነ፥ እንደ ጠላት መታኋችሁ፤ ያለ ርኅራኄም ቀጣኋችሁ።
ይህም የሆነው ገደብ በሌለው የአምንዝራይቱ ፍትወት ምክንያት ነው፤ እርስዋ በመተት እመቤትነትና በቊንጅናዋ የምታታልልና መንግሥታትን በዝሙትዋ፥ ሕዝቦችን በጥንቈላዋ የምትማርክ ነች።