ኢሳይያስ 21:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሠራተኞች የሥራ ውል እንደሚያልቅ ልክ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የቄዳር ነገዶች ክብር ይወገዳል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታም እንዲህ አለኝ፤ “በውል የተቀጠረ ሠራተኛ ቀን እንደሚቈጥር፣ የቄዳር ክብር በአንድ ዓመት ውስጥ ያበቃለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ብሎኛልና፦ እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንደ ገና እንዲህ ብሎኛልና፥ “እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ልጆች ክብር ሁሉ ይጠፋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እንዲህ ብሎኛልና፦ እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፥ |
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ! ስሙኝ፤ እኔ ጥቊር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ የመልኬ ጥቊረት እንደ ቄዳር ድንኳን ነው፤ ውበቴ ግን እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎች ነው።
አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአንድ ጊዜያዊ የቅጥር ሠራተኛ የሥራ ጊዜ እንደሚቋረጥ የሞአብ ክብርና ብዙ ሕዝቦችዋ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይዋረዳል፤ ከሕዝቧ የተረፉትም በጣም ጥቂቶችና ደካሞች ይሆናሉ።”
በረሓና በበረሓ የሚገኙ ከተሞች፦ እንዲሁም የቄዳር ሕዝቦች የሚኖሩባት መንደር ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ፤ የሴላዕ ከተማ ነዋሪዎች በደስታ ይዘምሩ፤ ከተራሮችም ጫፍ የእልልታ ድምፅ ያሰሙ።
የቄዳር የበግ መንጋዎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮት አውራ በጎችም ለመሥዋዕትነት ያገለግሉሻል፤ በመሠዊያም ላይ ለመሥዋዕትነት ለመቅረብ ተቀባይነት ይኖራቸዋል። የተከበረውን ቤተ መቅደሴንም አስጌጣለሁ።
ይህን የመሰለ ነገር ከዚህ በፊት ከቶ ተደርጎ እንደማያውቅ ታስተውሉ ዘንድ፥ እስቲ በስተ ምዕራብ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ሂዱ፤ በስተ ምሥራቅም ወደ ቄዳር ምድር መልእክተኞች ልካችሁ መርምሩ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ድል ስላደረጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር መንግሥታት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ተነሡ፤ በቄዳር ሕዝብ ላይ ዝመቱ፤ የምሥራቅንም ሕዝብ አጥፉ!