ኢሳይያስ 21:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ኤዶም የተነገረ ቃል ይህ ነው፤ አንድ ሰው ከኤዶም በኩል ሆኖ “ዘብ ጠባቂ ሆይ! ሌሊቱ መቼ ይነጋ ይሆን? ሌሊቱ ሊነጋ ምን ያኽል ጊዜ እንደ ቀረው ንገረኝ” ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ዱማ የተነገረ ንግር፤ አንዱ ከሴይር ጠርቶኝ፣ “ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው? ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ኤዶሚያስ የተነገረ ሸክም። አንዱ ከሴይር፦ “ጉበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ጉበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው?” ብሎ ጠራኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ኤዶምያስ የተነገረ ነገር። አንዱ ከሴይር፥ “ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው?” ብሎ ጠራኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ኤዶሚያስ የተነገረ ሸክም። አንዱ ከሴይር፦ ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ብሎ ጠራኝ። |
እንዲህም በማለት አዘዛቸው፥ “ለጌታዬ ለዔሳው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ ‘ታማኝ አገልጋይህ እኔ ያዕቆብ እስከ አሁን የቈየሁት ከላባ ጋር እንደ ነበር ልነግርህ እወዳለሁ፤
እግዚአብሔር ሆይ! ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፤ “እስከ መሠረትዋ አፈራርሳችሁ ጣሉአት!” እያሉ መጮኻቸውንም አስታውስ።
ዘብ ጠባቂውም “በእርግጥ የሌሊቱ ንጋት እየተቃረበ ነው፤ ነገር ግን ሌሊቱ ተመልሶ ይመጣል፤ እንደገና ጠይቀህ ለመረዳት ብትፈልግ ተመልሰህ ናና ጠይቅ” አለው።
ዘግየት ብሎም ንጉሥ ሴዴቅያስ መልእክተኛ ልኮ አስወሰደኝና በቤተ መንግሥቱ በግል ሲያነጋግረኝ “ከእግዚአብሔር የተነገረህ የትንቢት ቃል አለን?” ብሎ ጠየቀኝ። “አዎ፥ አለ!” ብዬ ንግግሬን በመቀጠል “አንተ ለባቢሎን ንጉሥ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አልኩት።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የኤዶም ሕዝብ በይሁዳ ላይ ጭካኔ የተሞላበት በቀል ፈጽመዋል፤ ይህንንም በማድረጋቸው በደለኞች ሆነዋል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ፥ እኔ አንተን ለእስራኤል ሕዝብ ጠባቂ አድርጌሃለሁ፤ እኔ የምሰጥህን ማስጠንቀቂያ ሁሉ ለእነርሱ ማስተላለፍ አለብህ፤
“የግብጽና የኤዶም ሰዎች በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ስለ ፈጸሙና ንጹሑንም ሕዝብ ስለ ገደሉ፥ ‘ግብጽ ወደ በረሓነት ትለወጣለች፤ ኤዶምም ሰው የማይኖርባት ምድረ በዳ ትሆናለች።’
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የጋዛ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ የሀገሩን ሕዝብ ሁሉ ከማረኩ በኋላ ለኤዶም ሰዎች አሳልፈው ሰጥተዋቸዋል።
የኤዶምን ኮረብታማ አገር ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታኽል እንኳ አልሰጣችሁምና በእነርሱ ላይ ጦርነት አታንሡ።