La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 19:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በግብጽ ባለጸጋም ሆነ ድኻ፥ ዝነኛ የሆነ ወይም ታዋቂነት የሌለው ምንም ነገር ማድረግ አይችልም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ራስም ይሁን ጅራት፣ የዘንባባ ዝንጣፊም ይሁን ደንገል፣ ለግብጽ የሚያደርጉላት አንዳች ነገር የለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ራስ ይሁን ጅራት፥ የዘንባባ ዝንጣፊ ይሁን ደንገል፥ ለግብጽ አንዳች ነገር ሊያደርጉላት አይችሉም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለግ​ብ​ፃ​ው​ያን ራስ ወይም ጅራት፥ መጀ​መ​ሪያ ወይም መጨ​ረሻ ያለው ሥራ የላ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ራስ ወይም ጅራት የሰሌን ቅርንጫፍ እንግጫ ቢሆን ሊሰራ የሚችል ሥራ ለግብጽ አይሆንላትም።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 19:15
7 Referencias Cruzadas  

ሠርተህ የምታፈራውን ትመገባለህ፤ ደስታና ሀብትም ታገኛለህ።


ተግቶ መሥራት ጥቅምን ያስገኛል፤ ወሬኛነት ግን ያደኸያል።


ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው አምላክ አልተመለሱም፤ ወይም የሠራዊት አምላክን የሚሹ ሆነው አልተገኙም።


ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፥ በወይን ተክል ላይም ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ዛፍም ምንም ፍሬ ባይሰጥ፥ በእርሻዎች ላይ ሰብል ቢጠፋ፥ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፥ በበረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፥


እነሆ በዚህ ምክንያት በተራሮች ላይ በእህል፥ በወይን፥ በዘይት፥ ምድር በምታበቅለው ሁሉ ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶች፥ በሥራቸውም ውጤት ሁሉ ላይ ድርቅን አመጣለሁ።”