ኢሳይያስ 19:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ንጉሥ ሆይ! እነዚያ ብልኆች አማካሪዎችህ የት አሉ? የሠራዊት አምላክ በግብጽ ላይ ያቀደውን ይንገሩህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእናንተ ጠቢባን አሁን የት አሉ? የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በግብጽ ላይ ያሰበውን ነገር፣ እስኪ ያሳዩአችሁ፤ ያሳውቋችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንስ ጥበበኞችህ የት አሉ? አሁን ይንገሩህ፤ የሠራዊት ጌታ በግብጽ ላይ ያሰበውን ይወቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን ጥበበኞችህ የት አሉ? አሁን ያብስሩህ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ ያሰበውን እስኪ ይንገሩህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንሳ ጥበበኞችህ የት አሉ? አሁን ይንገሩህ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ ያሰበውን ይወቁ። |
እንደ እኔ ያለ ማነው? እስቲ ካለ ይናገር፤ እስቲ ማስረጃውን በፊቴ ያቅርብ፤ ወደፊት የሚሆነውን አስቀድሞ የተናገረ ማነው? እስቲ ወደፊት የሚሆነውን ይናገር።
“በእጃችሁ የሠራችኋቸው አማልክት እስቲ የት አሉ? የሚችሉ ከሆነ መከራ ሲደርስባችሁ ተነሥተው ያድኑአችሁ፤ ይሁዳ ሆይ! ከተሞችህ ብዙዎች በሆኑ መጠን አማልክትህም በዝተዋል።”
በዚህ ምክንያት በቅዱስ መጽሐፍ ስለ ግብጽ ንጉሥ “በአንተ ኀይሌን ለማሳየትና ስሜም በዓለም ሁሉ ላይ እንዲታወቅ ለማድረግ አንተን አንግሼሃለሁ” የሚል ቃል ተጽፎአል።
ከዚህ በኋላ ዘቡል እንዲህ አለው፤ “ያ ሁሉ ፉከራህ አሁን የት ደረሰ? ‘አቤሜሌክ የተባለውን ሰው የምናገለግለው ለምንድን ነው?’ ብለህ የጠየቅህ አንተ አልነበርክምን? በማፌዝ ስታላግጥባቸው የነበርከው ሰዎች እነሆ፥ እነዚህ ናቸው፤ በል ወጥተህ ጦርነት ግጠማቸው፤”