ኢሳይያስ 19:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሸማኔዎች ግራ ይጋባሉ፤ ደመወዝተኞችም እየጮኹ ያለቅሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልብስ ሠሪዎች ያዝናሉ፤ ደመወዝተኞችም ልባቸው ይሰበራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሸማኔዎችዋም ሁሉ ቅስማቸው ይሰበራል፥ የደመወዘኞችም ልብ ይሰበራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነርሱም የሚሠሩ ይሠቃያሉ፤ በሐር ኩብ የሚነግዱ ሁሉ ይቀልጣሉ፤ ልቡናቸውም ያዝናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደገፋዎችዋም ሁሉ ይሰባበራሉ፥ የደመወዘኞችም ነፍስ ትተክዛለች። |
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አሮን በትሩን ወስዶ በግብጽ ምድር በሚገኙት ወንዞች፥ ቦዮችና ኲሬዎች ሁሉ ላይ እንዲዘረጋ ንገረው፤ በዚያን ጊዜ ውሃው ሁሉ ተለውጦ ደም ይሆናል፤ ከእንጨትና ከድንጋይ በተሠሩት የውሃ ማጠራቀሚያ ዕቃዎች እንኳ ሳይቀር በግብጽ ምድር የሚገኘው ውሃ ሁሉ ደም ይሆናል።”
እግዚአብሔርም ሙሴን “ጓጒንቸሮች ወጥተው መላውን የግብጽ ምድር ይሸፍኑ ዘንድ በወንዞች፥ በመስኖ ቦዮችና በኲሬዎች ሁሉ ላይ በትሩን እንዲዘረጋ ለአሮን ንገረው” አለው።
ይህች የምትወርሳት ምድር ከዚህ በፊት እንደ ነበርክባት እንደ ግብጽ ምድር አይደለችም። በግብጽ ምድር እህል ከዘራህ በኋላ እንደ ጓሮ አትክልት ማሳውን ውሃ ለማጠጣት ቦዩን በእግርህ አማካይነት ትቈጣጠረው ነበር።