“እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ! የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው! የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤ የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።
ኢሳይያስ 10:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያንም ጊዜ እናንተን ከአሦራውያን የጭቈና አገዛዝ ነጻ አወጣችኋለሁ፤ ከዚያን በኋላ የአገዛዝ ቀንበራቸው ከውፍረታችሁ የተነሣ ይሰበራል እንጂ በእናንተ ጫንቃ ላይ እንደተጫነ አይቀርም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ሸክማቸው ከትከሻህ፣ ቀንበራቸውም ከዐንገትህ ላይ ይነሣል፤ ከውፍረትህም የተነሣ ቀንበሩ ይሰበራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን ሸክማቸው ከትከሻህ፤ ቀንበራቸውም ከዐንገትህ ላይ ይነሣል፤ ከውፍረትህም የተነሣ ቀንበሩ ይሰበራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ቀንበሩ ከጫንቃህ፥ ፍርሀቱም ከአንተ ላይ ይወርዳል፤ ቀንበሩም ከጫንቃህ ወርዶ ይሰበራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ሸክሙ ከጫንቃህ ቀንበሩም ከአንገትህ ላይ ይወርዳል፥ ቀንበሩም ከውፍረት የተነሣ ይሰበራል። |
“እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ! የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው! የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤ የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።
እግዚአብሔር ቀብቶ ያነገሠውን እንደሚረዳ አሁን ዐውቃለሁ፤ በቀኝ እጁ ታላቅ ድልን በማቀዳጀት ከተቀደሰው ቦታ ከሰማይ ለጸሎቱ መልስ ይሰጠዋል።
አንተ መልካሙን ነገር ትወዳለህ፤ ክፉውን ነገር ትጠላለህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤ ከሌሎች ነገሥታትም ይበልጥ የደስታን ዘይት ቀባህ።
አሦራውያንን ለእስራኤል በሰጠኋት ምድሬ ላይ እደመስሳቸዋለሁ፤ በተራሮቼም ላይ እረግጣቸዋለሁ፤ ሕዝቤንም ከአሦራውያን የአገዛዝ ቀንበርና ከነበረባቸውም ከባድ ሸክም ነጻ አወጣቸዋለሁ።
ዘር በምትዘሩበት ጊዜ ቡቃያችሁን ለማሳደግና ብዙ መከር እንድታገኙ ለማድረግ እግዚአብሔር ዝናብን ይልክላችኋል፤ ከብቶቻችሁም ብዙ የመሰማሪያ ቦታ ያገኛሉ።
ምርኮኛይቱ ኢየሩሳሌም ሆይ! ተነሥተሽ ትቢያሽን አራግፊ፤ በዙፋን ላይም ተቀመጪ፤ እናንተም የጽዮን ምርኮኞች ሆይ! የታሰራችሁበትን ሰንሰለት ከአንገታችሁ ፍቱ።
ለማይጠቅም ምግብ ገንዘባችሁን ለምን ታወጣላችሁ? ለማያጠግብ ነገር ጒልበታችሁን ለምን ታባክናላችሁ? አሁንም በጥንቃቄ አድምጡኝና መልካም የሆነውን ምግብ ብሉ፤ በምርጥ ምግብም ራሳችሁን አስደስቱ።
በቀድሞ ዘመን ምድያማውያንን ድል እንዳደረግህ ሁሉ፥ አሁንም በሕዝብህ ላይ የተጫነውን የአገዛዝ ቀንበርና በትከሻቸው ላይ የተቃጣውን በትር ሰባበርክ፤ ሕዝብህን በማስጨነቅ ይገዛ የነበረውን ድል አደረግህ።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ያ ቀን በደረሰ ጊዜ በሕዝቤ ጫንቃ ላይ የተጫነውን የአገዛዝ ቀንበር እሰብራለሁ፤ ሰንሰለታቸውንም አስወግዳለሁ፤ ከዚያን በኋላ ለባዕዳን ሕዝብ ባሪያዎች አይሆኑም፤
የግብጽን ኀይል በመሰባበር የሚመኩበትን ብርታት በማስወግድበት ጊዜ ጣፍናስ በጨለማ ትጋረዳለች፤ ግብጽ በደመና ትሸፈናለች፤ የከተሞችዋ ኗሪዎችም ተማርከው ይወሰዳሉ።
ይህም እግዚአብሔር አሮንንና ልጆቹን ካህናት አድርጎ በሾመበት ቀን ለእግዚአብሔር ከቀረበው ከሚቃጠል መሥዋዕት ለካህናት ድርሻ ሆኖ የተለየ ነው፤
“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታትን፥ ለዕውሮች ማየትን እንዳውጅና የተጨቈኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤
“በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤
ከክርስቶስ የተቀበላችሁት መንፈስ በውስጣችሁ ስለሚኖር ሌላ አስተማሪ አያስፈልጋችሁም፤ እርሱ ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ የሚያስተምራችሁም እውነትን ነው እንጂ ሐሰትን አይደለም። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንዳስተማራችሁ በክርስቶስ ኑሩ።