ኢሳይያስ 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጥረቢያ እንጨት በሚቈርጥበት በባለቤቱ ላይ መነሣት ይችላልን? መጋዝስ በሚሰነጥቅበት ሰው ላይ መነሣት ይችላልን? እንዲሁም በትር በሚይዘው ሰው ላይ ኀይል አይኖረውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይኵራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፣ ዘንግም ራሱን ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኵራራ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፤ ዘንግም ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኩራራ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይነሣልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ሰው ላይ ይጓደዳልን? ይህም ዘንግ በሚመቱበት ላይ እንደ መነሣት፥ በትርም ዕንጨት አይደለሁም እንደ ማለት ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይመካልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ሰው ላይ ይጓደዳልን? ይህስ፥ በትር የሚያነሳውን እንደ መነቅነቅ ዘንግም እንጨት ያይደለውን እንደ ማንሳት ያህል ነው። |
እናንተ ሁሉን ነገር ትገለባብጣላችሁ። ሸክላ ሠሪው ከሸክላው አይበልጥምን? አንድ የተሠራ ሥራ ሠሪውን “አንተ አልሠራኸኝም” ይለዋልን? ወይስ ደግሞ የሸክላ ዕቃ ሸክላ ሠሪውን “ሥራህን አታውቅም” ይለዋልን?
ዐይንህን በትዕቢት አቅንተህ፥ ድምፅህን ከፍ አድርገህ በመጮኽ የተዳፈርከውና የተሳደብከው ማንን ይመስልሃል? የእስራኤልን ቅዱስ አይደለምን?’
ከሠሪው ጋር ለሚከራከር ወዮለት! እርሱ እኮ ከሸክላ ዕቃዎች እንደ አንዱ ነው፤ አንድ የሸክላ ሥራ ሸክላ ሠሪውን “ምንድን ነው የምታደርገው? እጀታውስ የት አለ?” ብሎ ሊጠይቅ ይችላልን?
“ያም ዘመን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሠ ነገሥት የራሳችሁን የጢማችሁንና የሰውነታችሁን ሁሉ ጠጒር ይላጫል።
ታዲያ ሊገድሉህ በሚመጡበት ጊዜ አሁንም ራስህን እንደ አምላክ ትቈጥር ይሆን? በገዳዮችህ እጅ ወድቀህ ስትገኝ ሰው እንጂ አምላክ ያለመሆንህ ይታወቃል።