“የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን በሥርዓት ያላነጹ ቢሆኑም እንኳ እነሆ በፍጹም ልባቸው አንተን በማምለክ ላይ ይገኛሉ፤ ስለዚህ በቸርነትህ ይቅር በላቸው!” ሲል ጸለየ፤
ዕብራውያን 9:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፍየሎችና የወይፈኖች ደምና ለመሥዋዕት የተቃጠለች ጊደር ዐመድ በረከሱ ሰዎች ላይ ሲረጭ ከሥጋዊ ርኲሰት አንጽቶ የሚቀድሳቸው ከሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የውጭ አካላቸው ይነጻ ዘንድ በረከሱ ሰዎች ላይ የሚረጨው የፍየሎችና የኰርማዎች ደም እንዲሁም የፍየሎችና የጊደር ዐመድ የሚቀድሳቸው ከሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኮርማዎችና የፍየሎች ደም፥ በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ፥ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የላምና የፍየል ደም፥ በረከሱትም ላይ የሚረጭ የጊደር አመድ፥ የሚያነጻና የረከሱትንም ሥጋቸውን የሚቀድሳቸው ከሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥ |
“የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን በሥርዓት ያላነጹ ቢሆኑም እንኳ እነሆ በፍጹም ልባቸው አንተን በማምለክ ላይ ይገኛሉ፤ ስለዚህ በቸርነትህ ይቅር በላቸው!” ሲል ጸለየ፤
ለመንጻት ሥርዓት በተዘጋጀው ውሃ እርጫቸው፤ በሰውነታቸው ላይ ያለውን ጠጒር ሁሉ እንዲላጩና ልብሳቸውንም አጥበው ራሳቸውን እንዲያነጹ አድርግ፤
ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል!
በመጀመሪያ ሙሴ የሕጉን ትእዛዞች ለሕዝቡ ሁሉ ነገረ፤ ከዚህ በኋላ የወይፈኖችንና የፍየሎችን ደም ከውሃ ጋር አድርጎ የሕጉን መጽሐፍና ሕዝቡን ሁሉ በሂሶጵና በቀይ የበግ ጠጒር ረጨ፤
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።