ዕብራውያን 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ ሁሉ በኋላ እምነታቸውን ቢክዱ እነርሱ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደገና ስለሚሰቅሉትና በይፋ ስለሚያዋርዱት እነርሱን ወደ ንስሓ መመለስ አይቻልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኋላ ግን የካዱትን እንደ ገና ወደ ንስሓ መመለስ አይቻልም፤ ምክንያቱም እነርሱ ለገዛ ጥፋታቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደ ገና ይሰቅሉታል፤ ያዋርዱታልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ ሁሉ በኋላ ቢክዱ፥ እነርሱ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደገና ስለሚሰቅሉትና ስለሚያዋርዱት፥ አይቻልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኋላም የካዱትን እንደ ገና ለንስሓ እነርሱን ማደስ አይቻልም፤ ራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና፥ ያዋርዱትማልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና። |
እርሱ የሚቃወሙትን ሰዎች በገርነት የሚያርም መሆን አለበት፤ ምናልባትም እውነትን ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ንስሓ የመግባትን ዕድል ይሰጣቸው ይሆናል።
ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል!
የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ።
እንግዲህ ሰማያትን ዘልቆ ወደ ላይ ወደ ሰማይ የወጣ ታላቅ የካህናት አለቃ ስላለን እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ፤ የካህናት አለቃውም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው።
እምነታቸውን የካዱትን ሰዎች ወደ ንስሓ መመለስ እንዴት ይቻላል? እነዚህ ሰዎች ከዚህ በፊት ብርሃን በርቶላቸው ነበር፤ ሰማያዊውንም ስጦታ ቀምሰው ነበር፤ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር ተካፋዮች ሆነው ነበር፤
የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ ይልቅ የጽድቅን መንገድ ሳያውቁ ቀርተው ቢሆን ኖሮ በተሻላቸው ነበር።
ማንም ሰው ወንድሙ ለሞት የማያደርስ ኃጢአት ሲሠራ ቢያየው ይጸልይለት፤ የሰውዬው ኃጢአት ለሞት የማያደርስ ከሆነ እግዚአብሔር ሕይወትን ይሰጠዋል። ነገር ግን ለሞት የሚያደርስ ኃጢአት አለ። ለእንዲህ ዐይነቱ ኃጢአት ይጸልይ አልልም።