ዕብራውያን 6:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደዚህም መቅደስ ኢየሱስ እንደ መልከጼዴቅ የክህነት ሹመት ለዘለዓለም የካህናት አለቃ ሆኖ ስለ እኛ ቀድሞ ገብቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ስፍራ ኢየሱስ ስለ እኛ ቀድሞ የገባበት ነው። እርሱም እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት ሆኗል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው ኢየሱስ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘለዓለም ሊቀ ካህናት ሆኖ ሐዋርያችን ኢየሱስ ከእኛ በፊት ወደ ገባባት መጋረጃም ውስጥ የምታስገባ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ። |
በዚህ ዐይነት እናንተም ከእስራኤላውያን ከምትቀበሉት ዐሥራት ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን ልዩ መባ ታቀርባላችሁ፤ ለእግዚአብሔር የምታመጡትን ይህን ልዩ መባ ለካህኑ አሮን ታስረክቡታላችሁ።
ማነው የሚፈርድ? ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈርድባቸዋልን? እርሱ ስለ እኛ የሞተ፥ ከሞት ተነሥቶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ የተቀመጠ፥ ስለ እኛም የሚማልድ ነው።
እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ትክክል ነው። በኀያል ቃሉ ዓለምን ሁሉ ደግፎ ይዞአል፤ ሰዎችንም ከኃጢአት ካነጻ በኋላ በሰማይ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦአል።
የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ።
ሁሉ ነገር በእርሱና ለእርሱ የተፈጠረው እግዚአብሔር ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት የመዳናቸውን መሪ ኢየሱስን በመከራ ፍጹም እንዲሆን እንዲያደርገው ተገባው።
ስለዚህ በሁሉም ነገር እንደ ወንድሞቹ መሆን ነበረበት፤ በዚህ ዐይነት የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ ብሎ እግዚአብሔርን ለማገልገል ታማኝና መሐሪ የካህናት አለቃ ሆነ።
እንግዲህ ሰማያትን ዘልቆ ወደ ላይ ወደ ሰማይ የወጣ ታላቅ የካህናት አለቃ ስላለን እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ፤ የካህናት አለቃውም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው።
እንግዲህ ከምንነጋገርባቸው ነገሮች ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማይ በልዑል እግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ የካህናት አለቃ አለን፤
እርሱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አንዴ በማያዳግም ሁኔታ የራሱን ደም ይዞ ገባ እንጂ የፍየሎችንና የወይፈኖችን ደም ይዞ አልገባም፤ በዚህም ዐይነት የዘለዓለም ቤዛን አስገኘልን።
ክርስቶስ የእውነተኛይቱ “መቅደስ” ምሳሌ ወደ ሆነችውና በሰው እጅ ወደተሠራችው ቅድስተ ቅዱሳን አልገባም፤ እርሱ አሁን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት ወደ ሰማይ ገባ።