እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈጸም አስበናል፤ በዚህም መሠረት ቃል ኪዳን እንድትገባልን የምንፈልገው፥
ዕብራውያን 6:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ውሳኔው የማይለወጥ መሆኑን ለማስረዳት ፈልጎ ለተስፋው ወራሾች ተስፋውን በመሐላ አጸናላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የማይለወጥ ዐላማውን ለተስፋው ቃል ወራሾች ግልጽ ለማድረግ ስለ ፈለገ፣ በመሐላ አጸናው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም እግዚአብሔር የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም እግዚአብሔር ተስፋውን ለሚወርሱ ሰዎች ምክሩን እንደማይለውጥ ሊገልጥ ወደደ፤ እንደማይለውጥም በመሓላ አጸናው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም እግዚአብሔር፥ የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ፥ እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፤ |
እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈጸም አስበናል፤ በዚህም መሠረት ቃል ኪዳን እንድትገባልን የምንፈልገው፥
ያ ሰው የእግዚአብሔር አገልጋዮች ወደሆኑት ዳኞች ዘንድ ይሂድ፤ የሰውዬውን እንስሳ አለመስረቁንም በመሐላ ያረጋግጥ፤ እንስሳው ያልተሰረቀ ከሆነ የእንስሳው ባለቤት ካሳ አይጠይቅ፤ እንስሳው የጠፋበትም ሰው ካሳ አይክፈል።
እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ! እነሆ ወደ አትክልት ቦታዬ ገባሁ፤ ከርቤዬንና የሽቶ አበባዎቼን ለቀምኩ፤ የማር ሰፈፌን ከወለላው ጋር ተመገብኩ፤ የወይን ጠጄንና ወተቴንም ጠጣሁ። ወዳጆቼ ሆይ! በፍቅር እስክትረኩ ድረስ ብሉ፥ ጠጡ።
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ።
ክፉዎች አካሄዳቸውን፥ ኃጢአተኞች ክፉ ሐሳባቸውን ይተዉ፤ ምሕረቱ ብዙ ስለ ሆነ ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ።
እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን የእርሱ ወራሾች ነን፤ ከክርስቶስም ጋር እንወርሳለን፤ አሁን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች ብንሆን በኋላ የክብሩ ተካፋዮች እንሆናለን።
ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ።
በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።
መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤
እናንተም ባሎች! ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ከእናንተ ይልቅ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑና ከእናንተም ጋር የሕይወትን ጸጋ ስለሚወርሱ አክብሩአቸው፤ በዚህ ዐይነት ለጸሎታችሁ መሰናክል የሚሆን ነገር አይኖርም።