ዕብራውያን 3:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ባለማመናቸው ምክንያት መሆኑን እናያለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ካለማመናቸው የተነሣ እንደ ሆነ እንረዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ባለማመናቸው ጠንቅ ሊገቡ እንዳልተቻላቸው እናያለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላመኑምና፥ ለመግባት እንዳልቻሉ እነሆ፥ እናያለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባለማመናቸውም ጠንቅ ሊገቡ እንዳልተቻላቸው እናያለን። |
ይህም ሆኖ የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግና የምትሄዱበትን መንገድ ለማሳየት ቀን በደመና ሌሊት በእሳት፥ በፊታችሁ በሚሄደው በአምላካችሁ በእግዚአብሔር አልተማመናችሁም።
በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን ይህ ምስክርነት በልቡ ውስጥ አለ፤ እግዚአብሔርን የማያምን ግን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውን ምስክርነት ባለማመኑ ሐሰተኛ አድርጎታል።
ይህን ሁሉ አስቀድማችሁ አንድ ጊዜ የምታውቁት ቢሆንም እንኳ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አውጥቶ እንዳዳነና ያላመኑትንም በኋላ እንዳጠፋቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።