ዕብራውያን 3:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ በዚያ በዐመፃው ጊዜ እንዳደረጋችሁት ዐይነት ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ” ተብሎ እንደ ተነገረው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም፣ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣ በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣ አሁንም ልባችሁን አታደንድኑ” እንደ ተባለው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት፥ በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ፤” እንደተባለው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዛሬ ቃሉን ብትሰሙ እነዚያ እንደ አሳዘኑት ጊዜ ልባችሁን አታጽኑ” ብሎአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እየተባለ፦ ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት፥ በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ። |
ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል!
ይህም አስቀድሞ እንደተባለው “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ፥ ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ።” ሲል እግዚአብሔር ከብዙ ዘመን በኋላ በዳዊት አማካይነት በተናገረው ቃል “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ቀን በመወሰኑ ተረጋግጦአል።