ዕብራውያን 13:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድማችን ጢሞቴዎስ ከእስር ቤት እንደ ወጣ እንድታውቁ እወዳለሁ፤ በቶሎ ወደዚህ ከመጣ ከእርሱ ጋር ወደ እናንተ መጥቼ አያችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ ታውቁ ዘንድ እፈልጋለሁ፤ ቶሎ ከመጣ፣ ከርሱ ጋራ ላያችሁ እመጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ እወቁ፤ ቶሎ ብሎም ቢመጣ ከእርሱ ጋር አያችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድማችን ጢሞቴዎስ ከእኛ ወደ እናንተ እንደ ተላከ ዕወቁ፤ ፈጥኖ ከመጣ አያችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ እወቁ፥ ቶሎ ብሎም ቢመጣ ከእርሱ ጋር አያችኋለሁ። |
ስለዚህ ይህን የተሰበሰበውን የገንዘብ ርዳታ ወደ ኢየሩሳሌም ወስጄ የማስረከብ ሥራዬን ከፈጸምኩ በኋላ በእናንተ በኩል አድርጌ ወደ እስፔን እሄዳለሁ።
ወንድማችንንና የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን፥ የክርስቶስን መልካም ዜና በማብሠር የሥራ ጓደኛችንን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፤ የላክንላችሁም እንዲያጸናችሁና በእምነት እንድትበረቱ እንዲመክራችሁ ነው፤
የእምነትን መልካም ጦርነት ተዋጋ፤ አንተ ወደ እርሱ በተጠራህ ጊዜ በብዙ ምስክሮች ፊት ትክክለኛ ምስክርነትን የሰጠኸውን ዘለዓለማዊውን ሕይወት ያዝ።
እንግዲህ ስለ ጌታችን ለመመስከር አትፈር፤ ስለ እርሱ በታሰርኩት በእኔም አትፈር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በሚሰጥህ ኀይል ስለ ወንጌል ከእኔ ጋር መከራን ተቀበል።
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ ከሆንኩ ከእኔ ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፥ ለተወደደው ወንድማችንና የሥራ ጓደኛችን ለሆነው ለፊልሞና፥
እኔም “ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ” አልኩት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ታላቁን መከራ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል፤