በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
ዕብራውያን 12:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስማቸው በሰማይ ወደተጻፈው፥ የቤተ ክርስቲያን የበኲር ልጆች ወደሆኑት ወደ አማኞች ጉባኤ፥ የሁሉ ፈራጅ ወደ ሆነው አምላክና ፍጹምነትን ወዳገኙት የጻድቃን ነፍሳት ቀርባችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈው ወደ በኵራት ማኅበር ቀርባችኋል፤ የሁሉ ዳኛ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር፣ ፍጹምነትን ወዳገኙት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅበረ በኵርም፥ ሁሉን ወደሚገዛም ወደ እግዚአብሔር፥ ወደ ፍጹማን ጻድቃንም ነፍሳት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ |
በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
“ከእስራኤል ሕዝብም ሆነ ከእንስሶቹ በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእኔ መሆን ይገባዋል፤ ስለዚህ በኲር ሆኖ የተወለደውን ሁሉ ለእኔ እንዲሆን ቀድሰው።”
እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።”
መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
አሁን በመስተዋት እንደምናየው ዐይነት በድንግዝግዝ እናያለን፤ በዚያን ጊዜ ግን በግልጥ እናያለን፤ አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን እግዚአብሔር እኔን የሚያውቀኝን ያኽል ሙሉ ዕውቀት ይኖረኛል።
ከማያፈቅራት ሚስቱ የተወለደ ቢሆንም እንኳ ለበኲር ልጁ የሚሰጠው ድርሻ ከሌሎቹ የነፍስ ወከፍ ድርሻ በእጥፍ ከፍ ያለ መሆን አለበት፤ ስለዚህም ያ ሰው ልጁ በመጀመሪያ በመወለዱ በኲር መሆኑን ተረድቶ የብኲርና ድርሻውን ሊሰጠው ይገባል።
አንተም እዚያ ያለኸው ታማኝ የሥራ ጓደኛዬ እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ፤ እነዚህ ሴቶች ከእኔ ጋር ከቀሌምንጦስና ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎችም የሥራ ጓደኞቼ ጋር በመሆን ወንጌልን በማዳረስ ረገድ ተጋድለዋል።
አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል፤ አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጐደለብኝን በሥጋዬ አሟላለሁ።
አቤል ከቃየል መሥዋዕት የበለጠውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረበው በእምነት ነው፤ እግዚአብሔር የአቤልን መባ በደስታ በተቀበለ ጊዜ አቤል በእምነቱ ጻድቅ መሆኑ ተመሰከረለት፤ አቤል ቢሞትም እንኳ በእምነቱ አማካይነት አሁንም እየተናገረ ነው።
እነርሱ ድንግሎች ስለ ሆኑ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ አልረከሱም፤ በጉ ወደሚሄድበትም ሁሉ ይከተሉታል። እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ ከሰዎች መካከል እንደ በኲራት የቀረቡ ናቸው።
ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ እንደ እነርሱ ገና የሚገደሉ፥ እንደእነርሱ አገልጋዮች የሆኑ የጓደኞቻቸውና የወንድሞቻቸው ቊጥር እስኪሞላ ድረስ ጥቂት ጊዜ ዐርፈው እንዲቈዩ ተነገራቸው።