ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤
ዕብራውያን 12:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በእጅ ወደሚዳሰሰው ወይም ወደሚቃጠለው ወደ ሲና ተራራ አልደረሳችሁም፤ ወደ ጭጋጉ፥ ወደ ጨለማውም፥ ወደ ዐውሎ ነፋሱም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፣ ወደ ጨለማው፣ ወደ ጭጋጉና ወደ ዐውሎ ነፋሱ አልደረሳችሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፥ ወደ ጭጋጉና ወደ ጨለማው፥ ወደ ዐውሎ ነፋሱ ገና አልደረሳችሁም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም፥ ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምፅም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፤ |
ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤
ስለዚህ “አባ! አባታችን ሆይ!” ብላችሁ የምትጠሩበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ በፍርሃት ለመኖር እንደገና የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም።
ሕግ የተቀረጸው በድንጋይ ጽላት በፊደል ነበር፤ ሕግ በተሰጠበትም ጊዜ የነበረው ብርሃን እየተወገደ የሚሄድ ቢሆንም እስራኤላውያን የሙሴን ፊት ትኲር ብለው ሊመለከቱት አልቻሉም፤ እንግዲህ ሞትን ያመጣ ሕግ በእንዲህ ዐይነት ክብር ከተገለጠ
እናንተ እሳቱን በመፍራት ወደ ተራራው መውጣት ስለ ፈራችሁ እኔ በዚያን ጊዜ እርሱ የሚለውን ሁሉ ልነግራችሁ በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ቆምኩ፤ “እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤