ዕብራውያን 12:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ የሚያስደስት አይመስልም፤ በኋላ ግን ለተለማመዱት ሰዎች ሰላም የሞላበትን የጽድቅ ፍሬ ያስገኝላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰዎች የጽድቅና የሰላም ፍሬ ያስገኝላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጊዜው ቅጣት ሁሉ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰላማዊ የጽድቅን ፍሬ ያፈራላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅጣት ሁሉ በጊዜው ያሳዝናል እንጂ ደስ አያሰኝም፤ በኋላ ግን ለተቀጡ ሰላምን ያፈራል፤ ጽድቅንም ያሰጣቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል። |
ከእንግዲህ ወዲህ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ይህንንም አክሊል ያ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጁ ጌታ በዚያን ቀን ይሰጠኛል፤ የሚሰጠውም ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእርሱን መገለጥ ለሚወድዱ ሁሉ ነው።
ኃጢአት ከማድረግ የማይቈጠብ ቅንዝረኛ ዐይን አላቸው፤ የኃጢአት መሥራት ፍላጎታቸው መቼም አይረካም፤ በእምነት ጸንተው ያልቆሙትን ሰዎች ያታልላሉ፤ ለገንዘብ ይስገበገባሉ። የተረገሙ ሰዎች ናቸው።