ከፍልስጥኤም ለሚመጡ መልእክተኞች የምንሰጠው መልስ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና መመሥረቱንና በሥቃይ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቡ መጠጊያ አግኝተው በሰላም እንዲኖሩ ማድረጉን እንነግራቸዋለን።
ዕብራውያን 11:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረገው ጽኑ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር ያቀዳትንና የሠራትን ከተማ ይጠባበቅ ስለ ነበር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም መሠረት ያላትን፣ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሠረት ያላትን ሠሪዋና ፈጣሪዋ እግዚአብሔር የሆነላትን ከተማ ደጅ ይጠኑ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና። |
ከፍልስጥኤም ለሚመጡ መልእክተኞች የምንሰጠው መልስ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና መመሥረቱንና በሥቃይ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቡ መጠጊያ አግኝተው በሰላም እንዲኖሩ ማድረጉን እንነግራቸዋለን።
ይህ እንደ ድንኳን ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊው ሥጋችን ሲፈርስ በሰው እጅ ሳይሆን በእግዚአብሔር የታነጸ ዘለዓለማዊ መኖሪያ በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።
አሁን ግን የሚበልጠውን፥ በሰማይ ያለውን አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው “አምላካችን” ብለው ቢጠሩት አያሳፍረውም።
እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ ቀርባችኋል፤ እርስዋ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ናት፤ በደስታ ወደተሰበሰቡት፥ በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት መላእክት ቀርባችኋል።