ዕብራውያን 10:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ተገቢ ዋጋን እከፍላለሁ” ያለው ማን መሆኑን እናውቃለን፤ እንዲሁም “እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤” ያለውን እናውቃለን፤ ደግሞም “ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔም ብድራትን እመልሳለሁ፥” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ዳግመኛም “እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም፦ ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል። |
“አሁንም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ለእናንተ ለእስራኤላውያን የምላችሁ ይህ ነው፤ በክፉ ሥራችሁ እያንዳንዳችሁን እቀጣለሁ፤ ስለዚህ ከምታደርጉት ክፋት ተመለሱ፤ አለበለዚያ ኃጢአታችሁ ያጠፋችኋል።
“ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ እናንተ ስለ መንጋዎቼ በመልካም በጎችና በክፉ በጎች በአውራ በጎችና በፍየሎች መካከል እፈርዳለሁ።
ወዳጆቼ ሆይ! ቊጣን ለእግዚአብሔር ተዉ እንጂ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ “የምበቀልና የበቀልንም ብድራት የምከፍል እኔ ነኝ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአል።
ባለሥልጣን ለአንተ መልካም እንዲያደርግ የተሾመ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፤ ባለሥልጣን ሰይፍ የታጠቀው በከንቱ ስላልሆነ ክፉ አድራጊ ከሆንክ ባለሥልጣንን ፍራ፤ እርሱ ክፉ አድራጊዎችን በመቅጣትና የእግዚአብሔርን በቀል በማሳየት እግዚአብሔርን ያገለግላል።
እያንዳንዱ በምድራዊ ሕይወቱ ላደረገው ክፉም ሆነ ደግ ነገር እንደየሥራው ዋጋውን ለመቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረብ አለብን።
የበቀል እርምጃ በመውሰድ ጠላቶችህን እንዳትገድል የጠበቀህ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ እኔ አሁን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ጠላቶችህና አንተን ለመጒዳት የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤
በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ራሱ ሳኦልን ይገድለዋል፤ የሚሞትበት ጊዜ ደርሶ፥ አለበለዚያም በጦርነት መሞቱ አይቀርም፤