ኢዩም “ኤልዛቤልን ወደታች ወርውሩአት!” አላቸው፤ እነርሱም አንሥተው በወረወሩአት ጊዜ ደምዋ በግንቡና በፈረሶች ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በሬሳዋ ላይ ፈረሶቹንና ሠረገላውን ነዳበት፤
ዕብራውያን 10:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፣ የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ተራ ነገር የቈጠረ፣ የጸጋንም መንፈስ ያክፋፋ እንደ ምን ያለ የባሰ ቅጣት ይገባው ይመስላችኋል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፥ የተቀደሰበትን ያንን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቆጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያስቆጣ፥ ቅጣቱ እጅግ የከፋ እንዴት የማይሆን ይመስላችኋል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ልጅ የከዳ፥ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቈጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? |
ኢዩም “ኤልዛቤልን ወደታች ወርውሩአት!” አላቸው፤ እነርሱም አንሥተው በወረወሩአት ጊዜ ደምዋ በግንቡና በፈረሶች ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በሬሳዋ ላይ ፈረሶቹንና ሠረገላውን ነዳበት፤
ከዚህ በኋላ ሙሴ በገበቴ ያለውን ደም ወስዶ በሕዝቡ ላይ በመርጨት “ይህ እንግዲህ እግዚአብሔር እነዚህን ሁሉ ትእዛዞች በሰጣችሁ ጊዜ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን የሚያጸናበት ደም ነው” አለ።
አንተ ግን ሳትቀበር በእግር እንደሚረጋገጥ የዛፍ ቅጠል የተጣልክ ሆነሃል፤ ሬሳህም በጦርነት ላይ በሞቱ ሰዎች ሬሳ ተሸፍኖአል፤ ከእነርሱም ሬሳ ጋር በድንጋያማ ጒድጓድ ውስጥ ተጥሎ ተረግጦአል።
“ኤርምያስ ሆይ! ገና በእናትህ ማሕፀን እንድትፀነስ ከማድረጌ በፊት ዐውቄሃለሁ፤ ከመወለድህም በፊት አንተን በመለየት ለሕዝቦች ነቢይ አድርጌ ሾሜሃለሁ።”
“እግዚአብሔር ወታደሮቻችንን ከእኛ አስወገደ፤ የጐልማሶቻችንን ኀይል ለማድቀቅ የጦር ሠራዊት ላከብን፤ እግዚአብሔር ባልተደፈረችው ከተማ የሚኖረውን ሕዝባችንን በወይን መጭመቂያ እንደሚረገጥ የወይን ዘለላ ረገጣቸው።
ከዚያ በኋላ አንድ ቅዱስ ሲናገር ሰማሁ፤ ሌላው ቅዱስ ደግሞ ለተናገረው ቅዱስ እንዲህ አለው፦ “እነዚህ በራእዩ የታዩት ነገሮች የሚፈጸሙበት ጊዜ መቼ ነው? ጥፋትን የሚያስከትለው ዐመፅና የዘወትርን መሥዋዕት ተክቶ የሚቈየው እስከ መቼ ነው? ቤተ መቅደሱና የሰማይ ሠራዊት ተላልፈው በመሰጠት ተረግጠው የሚቈዩትስ እስከ መቼ ነው?”
ጠላቴም ይህን ሁሉ ያያል፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ይለኝ የነበረው ጠላቴ ኀፍረትን ይከናነባል፤ እኔ የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ በመንገድ ዳር እንዳለ ጭቃ ሲረገጥም እመለከታለሁ።
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
የተቀደሰውን ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቋችሁንም በዐሣማዎች ፊት አትጣሉ፤ ዐሣማዎቹ ዕንቋችሁን በእግራቸው ይረግጡታል፤ ውሾቹም ተመልሰው ይነክሱአችኋል።
“በሰው ልጅ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ቢኖር በደሉ ይቅር ይባልለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ቢኖር ግን በደሉ ይቅር አይባልለትም።
ታዲያ፥ አብ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስለ አለ ስለምን ‘በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ትናገራለህ’ ትሉታላችሁ?
“እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር አድርጎለታል” የሚል ተጽፎአል፤ ነገር ግን “ሁሉ ነገር በሥልጣኑ ሥር ሆኖአል” ሲባል ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር ያደረገለትን እግዚአብሔር አብን አይጨምርም።
ከእናንተም አንዳንዶቻችሁ እንዲሁ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ከኃጢአት ታጥባችኋል፤ ለእግዚአብሔር የተለየ ቅዱስ ሕዝብ ሆናችኋል፤ ጸድቃችኋልም።
ያንን የሚናገረውን አንቀበልም እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ እግዚአብሔር በሰው አማካይነት ከምድር ሲናገራቸው አንሰማም ያሉት ካላመለጡ፥ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረንን ባንቀበል እንዴት እናመልጣለን!
ሰዎችን ቅዱሳን የሚያደርጋቸውና በእርሱ ቅዱሳን የሆኑትም ሰዎች የአንድ አባት ልጆች ናቸው፤ በዚህ ምክንያት ኢየሱስ እነርሱን “ወንድሞቼ” ብሎ ለመጥራት አያፍርም።
ታዲያ፥ እኛ ይህን ታላቅ መዳን ችላ የምንል ከሆንን እንዴት እናመልጣለን? ይህን መዳን በመጀመሪያ ያበሠረው ጌታ ራሱ ነው፤ ከእርሱ የሰሙትም ሰዎች ይህንኑ አረጋግጠውልናል።
እንግዲህ ሰማያትን ዘልቆ ወደ ላይ ወደ ሰማይ የወጣ ታላቅ የካህናት አለቃ ስላለን እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ፤ የካህናት አለቃውም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው።
እምነታቸውን የካዱትን ሰዎች ወደ ንስሓ መመለስ እንዴት ይቻላል? እነዚህ ሰዎች ከዚህ በፊት ብርሃን በርቶላቸው ነበር፤ ሰማያዊውንም ስጦታ ቀምሰው ነበር፤ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር ተካፋዮች ሆነው ነበር፤
ከዚህ ሁሉ በኋላ እምነታቸውን ቢክዱ እነርሱ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደገና ስለሚሰቅሉትና በይፋ ስለሚያዋርዱት እነርሱን ወደ ንስሓ መመለስ አይቻልም።