ዕብራውያን 10:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሙሴን ሕግ የጣሰ ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሰከሩበት ያለ ምሕረት በሞት ይቀጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሙሴን ሕግ የናቀ ማንኛውም ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሰከሩበት ያለ ምሕረት ይገደል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሙሴን ሕግ የተላለፈ ሰው “በሁለት እና በሦስት ምስክሮች ምስክርነት” ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሙሴ ሕግ የተላለፈ ቢኖር ሁለት፥ ወይም ሦስት ምስክሮች ከመሰከሩበት ያለ ምሕረት ይሞታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤ |
ታዲያ ትእዛዜን የናቅኸው ስለምንድን ነው? ይህንንስ ክፉ ነገር ለምን አደረግህ? ኦርዮን በጦር ሜዳ አስገደልከው፤ ንጹሑን ሰው ዐሞናውያን እንዲገድሉት አደረግህ፤ ሚስቱንም ወሰድክ!
የዛፍ ቅርንጫፎች በሚደርቁበትም ጊዜ ይሰባበራሉ፤ ሴቶችም ለእሳት ማገዶ ይለቅሙአቸዋል፤ ሕዝቡ ማስተዋል ስለ ጐደለው ፈጣሪ አምላኩ አይራራለትም፤ ምንም ምሕረት አያደርግለትም።
ያን ጊዜ አባቶችንና ልጆቻቸውን ሁሉንም እንደ ማድጋ እርስ በርሳቸው አጋጫቸዋለሁ፤ ምንም ዐይነት ሐዘኔታ፥ ርኅራኄ ወይም ምሕረት እነርሱን ከማጥፋት ሊያግደኝ አይችልም።”
“የአንድን ሰው ወንጀለኛነት ለማረጋገጥ አንድ ምስክር ብቻ አይበቃም፤ አንድ ሰው ወንጀለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች ያስፈልጋሉ።
ያንን የሚናገረውን አንቀበልም እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ እግዚአብሔር በሰው አማካይነት ከምድር ሲናገራቸው አንሰማም ያሉት ካላመለጡ፥ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረንን ባንቀበል እንዴት እናመልጣለን!