ዕብራውያን 10:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘወትር እየተገናኘን እርስ በርሳችን እንበረታታ እንጂ አንዳንዶች ማድረግ እንደ ለመዱት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም የጌታ መምጫ ቀን መቃረቡን እያስታወሳችሁ ይህን ነገር በይበልጥ አድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንዶች ማድረጉን እንደተዉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ እየተቃረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችን እንበረታታ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዳንዶችም ልምድ አድርገው እንደያዙት፥ መሰብሰባችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር፤ ይልቁንም የቀኑን መቅረብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌሎች ልማድ አድርገው እንደ ያዙት ማኅበራችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። |
አንድ ቀን ወደ ጸሎት ቦታ ስንሄድ ወደፊት የሚሆነውን ነገር በጥንቈላ የሚያናግር ርኩስ መንፈስ ያደረባት አንዲት አገልጋይ ልጃገረድ በመንገድ አገኘችን፤ ይህች ልጃገረድ በጥንቈላዋ ለአሳዳሪዎችዋ ብዙ ትርፍ ታስገኝላቸው ነበር።
ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን እንጀራ ቈርሶ በአንድነት ለመብላት ተሰበሰብን፤ ጳውሎስ በማግስቱ መሄድ ስለ ነበረበት ለተሰበሰቡት ሰዎች ይናገር ነበር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት አስረዘመ።
ስጦታችን መምከር ከሆነ እንምከር፤ ስጦታችን መለገሥ ከሆነ ከልብ እንለግሥ፤ ስጦታችን ማስተዳደር ከሆነ በትጋት እናስተዳድር፤ ስጦታችን ርኅራኄ ማድረግ ከሆነ ይህንኑ በደስታ እናድርግ።
ክርስቲያኖች በሚሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ ክርስቲያን በተለያዩ ቋንቋዎች ቢናገርና የማያውቁ ወይም የማያምኑ ሰዎች ቢመጡ ተናጋሪዎችን “እነዚህ ሰዎች አብደዋል” አይሉምን?
የእያንዳንዱ ሰው ሥራ የሚገለጥበት የፍርድ ቀን ይመጣል፤ በዚያን ቀን የእያንዳንዱ ሰው ሥራ ምን ዐይነት እንደ ሆነ በእሳት ተፈትኖ ይገለጣል።
ስለዚህ ወዳጆች ሆይ! ይህ ሁሉ የሚሆንበትን ቀን በመጠባበቅ ላይ ካላችሁ፥ ጌታ ያለ ነውር ወይም ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም እንዲያገኛችሁ በትጋት ኑሩ፤
አንዳንድ ሰዎች እንደሚመስላቸው ጌታ የተናገረውን የተስፋ ቃል ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም ሰው እንዳይጠፋ ፈልጎ ስለ እናንተ ይታገሣል።