ዕብራውያን 10:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፍቅርና በመልካም ሥራ ነቅተን እንድንኖር አንዱ ሌላውን ያሳስበው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳችንም ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተሳሰብ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍቅርና በበጎ ምግባርም ከባልንጀሮቻችን ጋር እንፎካከር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ |
እኔ ሁሉም እንዲድኑ የሌሎችን ጥቅም እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ ሰውን ሁሉ በማደርገው ነገር ሁሉ እንደማስደስት እናንተም እንዲሁ አድርጉ።
ታዲያ፥ ይህን የምላችሁ በማዘዝ አይደለም፤ ነገር ግን የሌሎችን የመስጠት ትጋት ከእናንተ ትጋት ጋር በማወዳደር የእናንተን ፍቅር እውነተኛነት ለማረጋገጥ ብዬ ነው።
“የዐካይያ ሰዎች ከዐለፈው ዓመት ጀምረው ለመርዳት ዝግጁዎች ናቸው” ብዬ በመቄዶንያ ሰዎች ዘንድ ስለ እናንተ የምመካው ትጋታችሁን ስለማውቅ ነው፤ የእናንተም ትጋት ሌሎችን አነሣሥቶአል።
ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ ለነጻነት ተጠርታችኋል፤ ነገር ግን አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል እንጂ ይህ ነጻነታችሁ የሥጋን ምኞት መፈጸሚያ ምክንያት አይሁን።
ወንድሞች ሆይ! ሰው ተሳስቶ አንዳች ጥፋት አድርጎ ቢገኝ መንፈሳውያን የሆናችሁት እናንተ እንዲህ ዐይነቱን ሰው በገርነት አቅኑት፤ ነገር ግን አንተም በዚህ ዐይነት ፈተና እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ።
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
በአምላካችንና በአባታችን ፊት እምነታችሁ የሚሠራውን፥ ለፍቅር የምታደርጉትንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ተስፋ በትዕግሥት መጠባበቃችሁን ሳናቋርጥ እናስታውሳለን።
ይህ የታመነ አባባል ነው። በእግዚአብሔር ያመኑ ሰዎች ለመልካም ሥራ እንዲተጉ ይህን ነገር ሁሉ በጥብቅ እንድታስገነዝብ እፈልጋለሁ፤ ይህም ነገር መልካምና ለእያንዳንዱ ሰው ጠቃሚ ነው።
ከእነርሱ ጋር አብራችሁ እንደ ታሰራችሁ ያኽል ሆናችሁ እስረኞችን አስታውሱ፤ እናንተም እንደ እነርሱ መከራ የምትቀበሉ ያኽል ሆናችሁ መከራ የሚቀበሉትን አስቡ።