ዕንባቆም 2:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሊባኖስ ላይ ያደረስከው ዐመፅ ይደርስብሃል፤ በእንስሶች ላይ ያደረግኸው ጥፋት ያስደነግጥሃል፤ ይህም የሚሆነው ሰውን ስለ ገደልክ፥ አገሮችንና ከተሞችን፥ በእነርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ ስላጠፋህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ያጥለቀልቅሃል፤ እንስሳቱን ማጥፋትህም ያስደነግጥሃል፤ የሰው ደም አፍስሰሃልና፤ አገሮችንና ከተሞችን በውስጣቸው የሚኖሩትንም ሁሉ አጥፍተሃልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰው ደም፥ በምድሪቱ፥ በከተማይቱና በእርሷም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ከተደረገው ዓመጽ የተነሣ፤ በሊባኖስ ላይ የተደረገው ዓመጽ ይከድንሃል፤ የአራዊትም ጥፋት ያስፈራቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰውንም ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ይከድንሃል፣ የአራዊትም አደጋ ያስፈራራሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውንም ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ይከድንሃል፥ የአራዊትም አደጋ ያስፈራራሃል። |
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።
“እናንተ ቀስተኞች ባቢሎንን ለመውጋት ዙሪያዋን ክበቡ፤ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ስለ ሠራች ፍላጾቻችሁንም ሁሉ በባቢሎን ላይ ወርውሩ፤ ለፍላጾቻችሁ አትሳሱ።
“የባቢሎን ምርኮኞችና በባቢሎን የነበሩ ስደተኞች ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። አምላካችን እግዚአብሔር በባቢሎናውያን ላይ ስለሚበቀለው በቀል የሚናገሩትን አድምጡ።”
በመግዛትና በመሸጥ ተግባር ትጣደፍ ነበር፤ ይህም ሁሉ ወደ ግፍ ሥራና ወደ ኃጢአት መራህ፤ በዚህም ምክንያት የተቀደሰውን ተራራዬን ለቀህ እንድትወጣ አስገደድኩህ፤ ከነዚያ ከሚያብረቀርቁ የከበሩ ድንጋዮች መካከል ጠባቂው ኪሩብ እያባረረ አስወጣህ።
እኔ ያን ዛፍ ወደ ሙታን ዓለም እንዲወርድ በማደርግበት ጊዜ አወዳደቁ የሚያሰማው ድምፅ ሕዝቦችን ሁሉ ያንቀጠቅጣል፤ ወደ ሙታን ዓለም የወረዱ የዔደን ዛፎችና የጥሩ መስኖ ውሃ የሚጠጡ የተመረጡ የሊባኖስ ዛፎች ሁሉ እርሱ ወደ ሙታን ዓለም በመውረዱ ደስ ይላቸዋል፤
“የግብጽና የኤዶም ሰዎች በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ስለ ፈጸሙና ንጹሑንም ሕዝብ ስለ ገደሉ፥ ‘ግብጽ ወደ በረሓነት ትለወጣለች፤ ኤዶምም ሰው የማይኖርባት ምድረ በዳ ትሆናለች።’
የብዙ ሕዝቦችን ንብረት ስለ ዘረፋችሁ ከእነርሱ የተረፉት የእናንተን ንብረት ይዘርፋሉ፤ ይህም የሚሆነው እናንተ ሰዎችን ስለ ገደላችሁ፥ ምድሪቱን ከተሞችንና በእነርሱ የሚኖሩትን ስላጠፋችሁ ነው።