ገላትያ 5:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመንፈስ ብትመሩ ግን የሕግ ተገዢዎች አትሆኑም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንፈስ ብትመሩ ግን፣ ከሕግ በታች አይደላችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንፈስ ብትመሩ ግን፥ ከሕግ በታች አይደላችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመንፈስን ፈቃድ የምትከተሉ ከሆናችሁ፥ ከኦሪት ወጥታችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም። |
የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል። እርሱ የሚናገረው የሰማውን እንጂ የራሱን ስላልሆነ እርሱ ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይነግራችኋል።
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእናንተም ሁኔታ እንደዚሁ ነው፤ እናንተ የክርስቶስ አካል ክፍል ስለ ሆናችሁ በሞት የመለየትን ያኽል ከሕግ ተለይታችኋል፤ ስለዚህ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ፍሬ እንድናፈራ ከሞት የተነሣው የክርስቶስ ወገኖች ሆናችኋል።
እንዲሁም ሕግ የተሠራው ለደጋግ ሰዎች እንዳልሆነ እናውቃለን፤ ሕግ የተሠራው ለዐመፀኞችና ለወንጀለኞች፥ እግዚአብሔርን ለማያመልኩና ለኃጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና መንፈሳዊ ነገርን ለሚንቁ፥ አባትንና እናትን ለሚገድሉና ለነፍሰ ገዳዮች፥