በጭንጫማ መሬት ላይ የወደቀውም ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ሰምተው በደስታ የሚቀበሉትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን እነርሱ የሚያምኑት ለጊዜው ነው፤ ሥር ስለሌላቸውም በፈተና ጊዜ ወዲያውኑ ይክዳሉ።
ገላትያ 4:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በፊት የነበራችሁ ደስታ ሁሉ የት ሄደ? ቢቻልስ ዐይኖቻችሁን እንኳ አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ እኔ ራሴ እመሰክርላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ያ ሁሉ ደስታችሁ የት ደረሰ? ቢቻላችሁ ዐይናችሁን ቢሆን እንኳ አውጥታችሁ የምትሰጡኝ እንደ ነበራችሁ እመሰክራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ መባረካችሁ የት አለ? ቢቻል ኖሮ ዐይኖቻችሁን እንኳ አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ እኔ እመሰክርላችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንስ ደስ ማሰኘታችሁ ወዴት አለ? ቢቻላችሁስ ዐይናችሁንም እንኳ ቢሆን አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ፥ እኔ ምስክራችሁ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ደስ ማሰኘታችሁ ወዴት አለ? ቢቻልስ ዓይኖቻችሁን አውጥታችሁ በሰጣችሁኝ ብዬ እመሰክርላችኋለሁ። |
በጭንጫማ መሬት ላይ የወደቀውም ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ሰምተው በደስታ የሚቀበሉትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን እነርሱ የሚያምኑት ለጊዜው ነው፤ ሥር ስለሌላቸውም በፈተና ጊዜ ወዲያውኑ ይክዳሉ።
ወደዚህ አሁን በእምነት ጸንተን ወደምንገኝበት ጸጋ የገባነው በእርሱ ስለ ሆነ በተስፋ የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች በመሆናችን እንመካለን።
ይህም የሆነው እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው በረከት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ለአሕዛብ እንዲደርስና እኛም እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያለውን መንፈስ ቅዱስን በእምነት እንድንቀበል ነው።
ምንም እንኳ ሕመሜ ፈተና ቢሆንባችሁ አልናቃችሁኝም ወይም አልተጸየፋችሁኝም፤ እንዲያውም የእግዚአብሔርን መልአክ እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ ተቀበላችሁኝ፤ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ ተቀበላችሁኝ።