በዚያን ጊዜ በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታ በራእይ “ሐናንያ!” ብሎ ጠራው፤ እርሱም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” አለ።
ገላትያ 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይም ከእኔ በፊት ሐዋርያት የነበሩትን ለመገናኘት ወደ ኢየሩሳሌም አልሄድኩም፤ ነገር ግን አስቀድሜ ወደ ዐረብ አገር ሄድኩ፤ እንደገናም ወደ ደማስቆ ተመለስኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኔ በፊት ሐዋርያት ወደሆኑትም ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፤ ነገር ግን ወዲያው ወደ ዐረብ አገር ሄድሁ፤ በኋላም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም ከእኔ በፊት ሐዋርያት ወደነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፤ ነገር ግን ወደ አረብ አገር ሄድሁ፤ እንደገና ወደ ደማስቆ ተመለስሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔ በፊት ወደ ነበሩት ወደ ሐዋርያትም ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፤ ነገር ግን ወደ ዐረብ ሀገር ሄድሁ፤ ዳግመኛም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔም በፊት ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥ ነገር ግን ወደ ዓረብ አገር ሄድሁ እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ። |
በዚያን ጊዜ በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታ በራእይ “ሐናንያ!” ብሎ ጠራው፤ እርሱም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” አለ።
የጌታንም መንገድ የሚከተሉትን ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ሲያገኝ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት የሚያስችል ደብዳቤ ለደማስቆ ምኵራቦች ተጽፎ እንዲሰጠው ሊቀ ካህናቱን ጠየቀ።
ሳውልም ከወደቀበት መሬት ተነሣ፤ ዐይኖቹን በገለጠ ጊዜ ግን ምንም ማየት አልቻለም፤ ስለዚህ ሰዎቹ እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ ወሰዱት።