ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር፤ እስጢፋኖስ በሞተበት ቀን በኢየሩሳሌም በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያት በቀር አማኞች ሁሉ ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ ምድር ተበተኑ።
ገላትያ 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀድሞ የአይሁድ እምነት ተከታይ በነበርኩበት ጊዜ እንዴት እንደ ኖርኩ ሰምታችኋል፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ከመጠን በላይ እያሳደድኩ ለማጥፋት እጥር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀድሞ በአይሁድ ሃይማኖት እንዴት እንደ ኖርሁ፣ የእግዚአብሔርንም ቤተ ክርስቲያን እንዴት በእጅጉ እንዳሳደድሁ፣ ለማጥፋትም እንዴት እንደ ጣርሁ ሰምታችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአይሁድ እምነት ተከታይ በነበርኩበት ጊዜ እንዴት እንደ ኖርኩ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ከመጠን በላይ አሳድድና አጠፋ እንደ ነበር ሰምታችኋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአይሁድ ሥርዐት ውስጥ በነበርሁ ጊዜ፥ የነበረውን የቀድሞ ሥራዬን ሰምታችኋል፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እጅግ አሳድድና መከራ አጸናባቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአይሁድ ሥርዓት በፊት እንዴት እንደ ኖርሁ ሰምታችኋልና፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ያለ ልክ አሳድድና አጠፋ ነበር፥ |
ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር፤ እስጢፋኖስ በሞተበት ቀን በኢየሩሳሌም በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያት በቀር አማኞች ሁሉ ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ ምድር ተበተኑ።
ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ይጥር ነበር፤ ከቤት ወደ ቤትም እየገባ ወንዶችና ሴቶች አማኞችን እየጐተተ ያወጣ ነበር፤ ወደ እስር ቤትም ያስገባቸው ነበር።
የሰሙትም ሁሉ፥ “ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሁሉ የሚያጠፋ የነበረ አይደለምን? ወደዚህስ የመጣው እነርሱን እያሰረ ወደ ካህናት አለቆች ለመውሰድ አይደለምን?” በማለት ይደነቁ ነበር።
ሳውል ወደ ኢየሩሳሌም በሄደ ጊዜ እዚያ ካሉት ደቀ መዛሙርት ጋር ለመደባለቅ ሞከረ፤ እነርሱ ግን የእርሱ በክርስቶስ ማመን እውነት ስላልመሰላቸው ሁሉም ፈሩት።
ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም ክርስቶስን የሰደብኩና ያሳደድኩ፥ ያዋረድኩም ብሆን፤ እርሱ ምሕረት አደረገልኝ፤ እርሱም ይህን ምሕረት ያደረገልኝ እኔ ይህን ሁሉ ያደረግኹት ባለማወቅና ባለማመን ስለ ነበረ ነው።