ኀላፊነታቸውም የአሮን ልጆች በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በሚያከናውኑት ተግባር መርዳት፥ የአደባባዩንና የክፍሎቹን እንክብካቤ መጠበቅ፥ ንዋያተ ቅድሳትን ማንጻት፥ እንዲሁም አጠቃላይ የሆነውን የቤተ መቅደሱን አገልግሎት ማከናወን ነው።
ዕዝራ 8:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ “እነሆ እናንተ ለቀድሞ አባቶቻችን አምላክ ለእግዚአብሔር የተለያችሁ ናችሁ፤ እንዲሁም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ሆነው የቀረቡት ከብርና ከወርቅ የተሠሩት ዕቃዎች ሁሉ ለቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር የበጎ ፈቃድ መባ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አልኋቸው፤ “እናንተና እነዚህ ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል፤ ብሩና ወርቁ ለአባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር የበጎ ፈቃድ ስጦታ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም አልኋቸው፦ “እናንተ ለጌታ ተቀድሳችኋል፥ ዕቃዎቹም ቅዱስ ናቸው፤ ብሩና ወርቁም ለአባቶቻችን አምላክ ለጌታ በበጎ ፈቃድ የቀረበ መባ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም “እናንተ ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል፤ ዕቃዎቹም ቅዱሳን ናቸው፤ ብሩና ወርቁም ለአባቶቻችን አምላክ ለእግዚአብሔር በፈቃድ የቀረበ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ “እናንተ ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል፤ ዕቃዎቹም ቅዱስ ናቸው፤ ብሩና ወርቁም ለአባቶቻችን አምላክ ለእግዚአብሔር በፈቃድ የቀረበ ነው፤ |
ኀላፊነታቸውም የአሮን ልጆች በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በሚያከናውኑት ተግባር መርዳት፥ የአደባባዩንና የክፍሎቹን እንክብካቤ መጠበቅ፥ ንዋያተ ቅድሳትን ማንጻት፥ እንዲሁም አጠቃላይ የሆነውን የቤተ መቅደሱን አገልግሎት ማከናወን ነው።
የእድሳቱ ሥራ ባለቀ ጊዜም ቀሪው ገንዘብ ለንጉሥ ኢዮአስና ለካህኑ ዮዳሄ ተሰጠ፤ እነርሱም በዚህ ወርቅ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎትና ለመሥዋዕት የሚውሉ ሳሕኖችንና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ገዙ። ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ ዘወትር በቤተ መቅደስ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር፤
እናንተ የቤተ መቅደስን ንዋያተ ቅድሳት የተሸከማችሁ! ከባቢሎን ውጡ፤ ከእርሱም ተለዩ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋም ወጥታችሁ ራሳችሁን አንጹ።
ያቀረባቸውም መባዎች እነዚህ ናቸው፦ በመቅደሱ ሚዛን መሠረት መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን አንድ ከብር የተሠራ ዝርግ ሳሕን፥ ከሰባ ሰቅል ብር የተሠራ አንድ ጐድጓዳ ሳሕን፥ ሁለቱም ለእህል ቊርባን በሚሆን ከዘይት ጋር በተቀላቀለ ደቃቅ ዱቄት የተሞሉ፥
ስለ ሌዊም ነገድ እንዲህ አለ፦ “ጌታ ሆይ! በቱሚምና በዑሪም አማካይነት በማሳና በመሪባ ውሃ ዘንድ ተከራክረህ ለፈተንካቸው ለአገልጋዮችህ ለሌዋውያን ፈቃድህን ግለጥ።