ሼሽባጻር ከሌሎቹ ስደተኞች ጋር ሆኖ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ ያመጣቸው ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎች ድምር 5400 ነበር።
ዕዝራ 6:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል አከበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምርኮኞቹ በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል አከበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምርኮኞቹም በመጀመሪያው ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አከበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምርኮኞቹም ልጆች በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምርኮኞቹም በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አደረጉ። |
ሼሽባጻር ከሌሎቹ ስደተኞች ጋር ሆኖ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ ያመጣቸው ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎች ድምር 5400 ነበር።
በዚያኑ ጊዜ ዳንኤል በንጉሡ ፊት ቀረበ፤ ንጉሡም እንዲህ አለው፦ “አባቴ ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ካመጣቸው ከይሁዳ ስደተኞች መካከል አንዱ የሆንክ ዳንኤል አንተ ነህን?