ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዐይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ።
ዕዝራ 6:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤተ መቅደሱን ሥራ የፈጸሙትም ዳርዮስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በስድስተኛው ዓመት አዳር ተብሎ የሚጠራው ወር በገባ በሦስተኛው ቀን ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ቤተ መቅደስ ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት አዳር ተብሎ በሚጠራው ወር በሦስተኛው ቀን ተጠናቀቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ቤት በንጉሡ በዳርዮስ መንግሥት በስድስተኛው ዓመት አዳር በሚባል ወር በሦስተኛው ቀን ተፈጸመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ቤት በንጉሡ በዳርዮስ መንግሥት በስድስተኛው ዓመት አዳር በሚባል ወር በሦስተኛው ቀን ተፈጸመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ቤት በንጉሡ በዳርዮስ መንግሥት በስድስተኛው ዓመት አዳር በሚባል ወር በሦስተኛው ቀን ተፈጸመ። |
ሰሎሞንም ኻያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ኻያ ሺህ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ በዚህም ዐይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረጉ።
ስለዚህም ሼሽባጻር መጥቶ መሠረቱን ጣለ፤ ከዚያም በኋላ የሕንጻው ሥራ እንዲቀጥል ተደርጎ፥ ይኸው እስከ አሁን በመሠራት ላይ ነው፤ ነገር ግን የቤተ መቅደሱ ሕንጻ ገና አልተፈጸመም።’
እኛ ባርያዎች ነበርን፤ አንተ ግን ባርያዎች ሆነን እንድንቀር አልተውከንም፤ አንተ የፋርስ ነገሥታት እንዲራሩልንና በሕይወት ነጻ ወጥተን ቀደም ሲል ፈርሶ የነበረውን ቤተ መቅደስህን እንደገና መልሰን እንድንሠራ፥ እዚህም በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሰላም እንድንኖር ፈቀድክልን።
ፈጣኖች የሆኑ ሯጮችም ይህን ዐዋጅ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ወደሚገኙት አገሮች ሁሉ እንዲያደርሱ ተላኩ፤ በዐዋጁም ውስጥ አዳር ተብሎ በሚጠራው በዐሥራ ሁለተኛው ወር፥ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን መላውን የአይሁድ ወጣት፥ ሽማግሌ፥ ሴት፥ ወንድ ሳይቀር ሕፃናትንም ጭምር እንዲገድሉ፥ እንዲያጠፉና እንዲደመሰሱ የሚያዝ ቃል ነበረበት፤ ንብረታቸውም ሁሉ እንዲዘረፍ ትእዛዝ ወጥቶ ነበር።
አርጤክስስ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፥ ኒሳን ተብሎ በሚጠራው የመጀመሪያው ወር ፑሪም ተብሎ የተሠየመው ዕጣ መጣል እንዲጀመርና አይሁድን ለማጥፋት የተጠነሰሰውን ሤራ በሥራ ላይ ለማዋል አመቺ የሚሆነው ወርና ቀን የትኛው እንደ ሆነ ተለይቶ እንዲታወቅ ትእዛዝ ሰጠ፤ በዕጣውም መሠረት አዳር ተብሎ የሚጠራው ዐሥራ ሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን እንዲሆን ተወሰነ።
ይህም ንጉሣዊ ትእዛዝ አዳር ተብሎ የሚጠራው ዐሥራ ሁለተኛ ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን፥ ማለትም አይሁድ እንዲገደሉ በታቀደበት ዕለት በመላው የፋርስ የንጉሠ ነገሥት ግዛት ሁሉ ሥራ ላይ እንዲውል ተወሰነ።
አዳር ተብሎ የሚጠራው ወር ዐሥራ ሦስተኛ ቀን እነሆ ደረሰ፤ ያም ዕለት የአይሁድ ጠላቶች ሁሉ አይሁድን በቊጥጥራቸው ሥር ስለ ማድረግ የወጣውን ንጉሣዊ ዐዋጅ ለመፈጸም የተዘጋጁበት ቀን ነበር፤ ነገር ግን ሁኔታው ተለውጦ አይሁድ በእነርሱ ላይ ድልን ተቀዳጁ።
አዳር ተብሎ በሚጠራው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በሱሳ የሚኖሩ አይሁድ እንደገና በአንድነት ተደራጅተው በተጨማሪ ሦስት መቶ ሰዎችን ገደሉ፤ ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ዘረፋ አላካሄዱም።
ይህም የሆነው አዳር የተባለው ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ነበር፤ በተከታዩ ዐሥራ አራተኛ ቀን ግን ምንም ግድያ ሳያካሄዱ የተድላ ደስታ ቀን አድርገውት ዋሉ።
በታናናሽ ከተሞች የሚኖሩ አይሁድ አዳር ተብሎ በሚጠራው ወር ዐሥራ አራተኛውን ዕለት የበዓል ቀን በማድረግ ሲበሉና ሲጠጡ እርስ በርሳቸውም አንዱ ለሌላው የምግብ ስጦታ ሲለዋወጡ የሚውሉት ስለዚህ ነው።
ዳርዮስ የፋርስ ንጉሥ በሆነ በሁለተኛው ዓመት፥ በስምንተኛው ወር እግዚአብሔር በዒዶ የልጅ ልጅ በበራክዩ ልጅ በነቢዩ በዘካርያስ አማካይነት የተናገረው ቃል ይህ ነው፤
“የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤተ መቅደስ መሠረት ጥለዋል፤ እጆቹም ይፈጽሙታል፤ ያን ጊዜ የሠራዊት አምላክ እኔን ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።