ዕዝራ 10:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሓሪም ጐሣ፦ ማዕሤያህ፥ ኤልያስ፥ ሸማዕያ፥ የሒኤልና ዑዚያ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከካሪም ዘሮች፤ መዕሤያ፣ ኤልያስ፣ ሸማያ፣ ይሒኤልና ዖዝያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሐሪም ልጆችም፦ ማዕሤያ፥ ኤልያ፥ ሽማዕያ፥ ይሒኤል፥ ዑዚያ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኤራም ልጆችም መሳሔል፥ ኤልያ፥ ሴሚያ፥ ያሔል፥ ዖዝያ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከካሪም ልጆችም፤ መዕሤያ፥ ኤልያስ፥ ሸማያ፥ ይሒኤል፥ ዖዝያ። |
ከዚህ የሚከተለው ደግሞ ከምርኮ የተመለሱ የካህናት ቤተሰብ ዝርዝር ነው፦ የኢያሱ ዘር የሆነው የይዳዕያ ቤተሰብ 973 የኢሜር ቤተሰብ 1052 የፓሽሑር ቤተሰብ 1247 የሓሪም ቤተሰብ 1017
የኢዮጼዴቅ ልጅ ኢያሱም ከወገኖቹ ካህናትና የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልም ከዘመዶቹ ጋር በመተባበር የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንደገና ሠሩ፤ የእግዚአብሔር ሰው ለሆነው ለሙሴ በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ በተጻፈውም መመሪያ መሠረት በዚያ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ ቻሉ።