ስለዚህ አለቆቻችን በዚሁ በኢየሩሳሌም ጉዳዩን ያጥኑት፤ ከዚህም በኋላ ባዕድ ሴት ያገባ ሁሉ እያንዳንዱ በሚሰጠው የቀጠሮ ቀን ከሚኖርባት ከተማ መሪዎችና ዳኞች ጋር እየመጣ ውሳኔውን ይቀበል፤ እግዚአብሔር የተቈጣበትም ሁኔታ ሁሉ በዚሁ ዐይነት ይበርዳል።”
ዕዝራ 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም በተነገረ ጊዜ መሹላምና ሻበታይ ተብሎ የሚጠራው አንድ ሌዋዊ ድጋፍ ከሰጡአቸው ከዐሣሔል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ከሆነው ከያሕዘያ በቀር ሌላ ተቃዋሚ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህንም ነገር የተቃወሙት ከሜሱላምና ከሌዋዊው ከሳባታይ ድጋፍ ያገኙት የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ብቻ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዐሣሄል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ያሕዝያ ብቻ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ምሹላምና ሌዋዊውም ሻብታይ ደገፏቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሐዝያ ስለዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤ ሜሱላምና ሌዋዊው ሰባታይም ይረዱአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ሜሱላምና ሌዋዊዉ ሳባታይ ረዱአቸው። |
ስለዚህ አለቆቻችን በዚሁ በኢየሩሳሌም ጉዳዩን ያጥኑት፤ ከዚህም በኋላ ባዕድ ሴት ያገባ ሁሉ እያንዳንዱ በሚሰጠው የቀጠሮ ቀን ከሚኖርባት ከተማ መሪዎችና ዳኞች ጋር እየመጣ ውሳኔውን ይቀበል፤ እግዚአብሔር የተቈጣበትም ሁኔታ ሁሉ በዚሁ ዐይነት ይበርዳል።”
ከምርኮ የተመለሱት ሁሉ ይህንኑ ዕቅድ ለመቀበል ተስማሙ፤ ስለዚህም ካህኑ ዕዝራ ከጐሣ መሪዎች መካከል መርጦ አስፈጻሚዎችን በመሾም ስም ዝርዝራቸውን መዝግቦ አኖረ፤ እነርሱም ዐሥረኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ጉዳዩን መመርመር ጀመሩ።
ዐዛርያ፥ ዕዝራ፥ መሹላም፥ ይሁዳ፥ ብንያም፥ ሸማዕያና ኤርምያስ ተብለው የሚጠሩት ካህናትም በሰልፍ አለፉ፤ ቀጥሎም እምቢልታ የሚነፉ ጥቂት ካህናትና እንዲሁም ዘካርያስ የዮናታን ልጅ የሸማዕያ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሚክያን ልጅ፥ የዛኩር ልጅ የአሳፍ ልጅ አለፉ።
የፓሴሕ ልጅ ዮዳሄ፥ የበሶድያ ልጅ መሹላም የይሻናን ቅጽር በር ሠሩ፤ ምሰሶዎችንም አቆሙለት፤ በሮችንም ገጠሙ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጁ።