ዘፀአት 8:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም የንጉሡ ቤተ መንግሥትና የመኳንንቱ ቤቶች ሁሉ በዝንብ መንጋ እንዲወረሩ አደረገ፤ መላዋም የግብጽ ምድር በዝንብ መንጋ ተበላሸች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲሁ አደረገ፤ አስጨናቂ የዝንብ መንጋ በፈርዖን ቤተ መንግሥትና በሹማምቱ ቤቶች ላይ ወረደ፤ መላው የግብጽ ምድር ከዝንቡ የተነሣ ተበላሽቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም፦ “ለጌታ አምላካችሁ በምድረ በዳ እንድትሠዉ እለቅቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ርቃችሁ አትሂዱ፥ ጸልዩልኝ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ አደረገ፤ የውሻው ዝንብም በፈርዖን ቤት፥ በሹሞቹም ቤቶች ውሰጥ፥ በግብፅም ሀገር ሁሉ መጣ፤ ምድሪቱም ከውሻው ዝንብ የተነሣ ጠፋች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንዲሁ አደረገ፤ በፈርዖንም ቤት፥ በባሪያዎቹም ቤቶች ውስጥ ብዙ የዝንብ መንጋ መጣ፤ በግብፅም አገር ሁሉ ላይ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ምድር ጠፋች። |
እምቢ ብትል ግን በአንተ፥ በመኳንንትህና በሕዝብህ ቤቶች የዝንብ መንጋ እልካለሁ፤ የግብጻውያን ቤቶችና የቆሙበት ምድር በዝንብ መንጋ የተሞላ ይሆናል።