ዘፀአት 6:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዕቆብ በኲር ልጅ ሮቤል፥ ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔጽሮንና ካርሚ የሚባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሮቤል ነገድ አባቶች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የየቤተ ሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፣ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ። እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባቶቻቸው ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው። የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ልጆች ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔፅሮንና ካርሚ፤ እነዚህ የሮቤል ወገኖች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባቶቻቸውም ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው። የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች ሄኖኅ፥ ፍሉስ፥ አስሮን፥ ከርሚ፤ እነዚህ የሮቤል ትውልድ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባታቸውም ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው። የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፦ ሄኖኅ፥ ፈሉስ፥ አስሮን፥ ከርሚ፤ እነዚህ የሮቤል ወገኖች ናቸው። |
የጐሣዎቻቸው አለቆች ዔፌር፥ ዩሽዒ፥ ኤሊኤል፥ ዓዝሪኤል፥ ኤርምያስ፥ ሆዳውያና ያሕዲኤል ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የታወቁ የጐሣ መሪዎችና ጀግኖች ወታደሮች ነበሩ።
ቶላዕ ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ዑዚ፥ ረፋያ፥ ይሪኤል፥ ያሕማይ፥ ዩብሳምና ሸሙኤል ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም የቶላዕ ጐሣ ቤተሰቦች አለቆችና ዝነኛ ወታደሮች ነበሩ፤ በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት የእነርሱ ዘሮች ብዛት ኻያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።
ቤላዕ አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ኤጽቦን፥ ዑዚ፥ ዑዚኤል፥ ያሪሞትና ዒሪ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም በጐሣዎቻቸው ውስጥ የቤተሰብ አለቆችና ዝነኛ ወታደሮች ነበሩ፤ ከእነርሱ ተወላጆች መካከል ዕድሜአቸው ለውትድርና አገልግሎት የደረሰ ኻያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ወንዶች ነበሩ።
የኤሁድ ዘሮች ናዕማን፥ አሒያና ጌራ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም በጌባዕ ይኖሩ ለነበሩት በኋላ ግን ከዚያ ተባረው ወደ ማናሐት ሄደው በዚያ ለኖሩ ቤተሰቦች አለቆች ነበሩ፤ ወደዚያም የመራቸው የዑዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበር።
እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን “እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር መርታችሁ እንድታወጡ እኔ ያዘዝኳችሁ መሆኔን ለእስራኤላውያንና ለግብጽ ንጉሥ ንገሩ” ብሎ አዘዛቸው።
ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ ማኅበሩን ሁሉ በአንድነት ሰብስበው በየነገዱና በየቤተሰቡ ከመደቡ በኋላ የሕዝብ ቈጠራ አደረጉ፤ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ስማቸው እየተመዘገበ ተቈጠሩ።
በምዕራብ በኩል የዮርዳኖስም ወንዝ ለሮቤል ነገድ የርስቱ ወሰን ነበር፤ እንግዲህ ለሮቤል ነገድ ቤተሰቦች ርስት ሆነው የተሰጡአቸው ከተሞችና መንደሮች እነዚህ ነበሩ።
ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የቤተሰብ አለቆች በከነዓን ምድር ለእስራኤላውያን አከፋፍለዋቸው የተቀበሉት ርስት ይህ ነው።
ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ የነገድ አለቆች በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ለእስራኤል ሕዝብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። በዚህም ዐይነት ምድሪቱን አከፋፍለው ጨረሱ።