በሉ አሁንም ወደ ሥራችሁ ተመለሱ! ከቶ ገለባ አይሰጣችሁም፤ ነገር ግን ቀድሞ የምትሠሩትን ያኽል ጡብ እየሠራችሁ ማስረከብ ይኖርባችኋል!” አላቸው።
ዘፀአት 5:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆች ቀድሞ የሚሠሩትን ያኽል ጡብ በየቀኑ መሥራት እንዳለባቸው በተረዱ ጊዜ በመከራ ላይ መውደቃቸውን ተገነዘቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ኀላፊዎችም፣ “በየቀኑ የምትሠሩት ሸክላ ቍጥሩ ቀድሞ ከሚሠራው ሸክላ ማነስ የለበትም” ተብሎ ሲነገራቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተረዱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች አለቆች፦ “ዕለት ዕለት ከምትሰሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታጉድሉ” በተባሉ ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች አለቆች ዕለት ዕለት ከምትሠሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታጕድሉ ባሉአቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች አለቆች፦ “ዕለት ዕለት ከምትሰሩት ከጡቡ ቁጥር ምንም አታጕድሉ!” ባሉአቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ። |
በሉ አሁንም ወደ ሥራችሁ ተመለሱ! ከቶ ገለባ አይሰጣችሁም፤ ነገር ግን ቀድሞ የምትሠሩትን ያኽል ጡብ እየሠራችሁ ማስረከብ ይኖርባችኋል!” አላቸው።
ነገር ግን ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን ያኽል አንድ ጡብ እንኳ ሳይጐድል እንዲያስረክቡ አድርጉ፤ ‘ለአምላካችን መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ ልቀቀን!’ እያሉ የሚነዘንዙኝ ብዙ የሚሠሩት ነገር ስለሌለ ነው፤
እንደገናም በዓለም ያለውን የፍርድ መጓደልና ግፍ ተመለከትኩ፤ የተገፉ ጭቊኖች የሚያጽናናቸው አጥተው ያለቅሱ ነበር፤ የፈላጭ ቈራጭነት ሥልጣን በገዢዎቻቸው እጅ ስለ ሆነ የሚረዳቸው አላገኙም።
በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።