ምሕረትህም ታላቅ በመሆኑ በዚያ ምድረ በዳ ይጠፉ ዘንድ አልተውካቸውም፤ ነገር ግን የደመናው ዐምድ በቀን ይመራቸው ነበር፤ የእሳቱ ዐምድ በሌሊት ያበራላቸው ነበር።
ዘፀአት 40:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጉዞአቸው ሁሉ እስራኤላውያን የሰፈሩበትን ቦታ ለቀው የሚንቀሳቀሱት ደመናው ከድንኳኑ ላይ በሚነሣበት ጊዜ ብቻ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእስራኤላውያን ጕዞ ሁሉ ደመናው ከማደሪያው ላይ በተነሣ ጊዜ፣ ይጓዙ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደመናው ከማደሪያው በሚነሣበት ጊዜ የእስራኤል ልጆች ወደሚጓዙበት ሁሉ ይሄዱ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመናውም ከድንኳኑ በተነሣ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በየነገዳቸው ይጓዙ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደመናውም ከማደሪያው በተነሣ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በመንገዳቸው ሁሉ ይጓዙ ነበር። |
ምሕረትህም ታላቅ በመሆኑ በዚያ ምድረ በዳ ይጠፉ ዘንድ አልተውካቸውም፤ ነገር ግን የደመናው ዐምድ በቀን ይመራቸው ነበር፤ የእሳቱ ዐምድ በሌሊት ያበራላቸው ነበር።
ደመናው ከድንኳኑ ላይ በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ሰፈራቸውን ለቀው ይጓዙ ነበር፤ ደመናውም በሚወርድበት ቦታ እንደገና ይሰፍሩ ነበር፤
ሁለት ቀንም ይሁን አንድ ወር፥ አንድ ዓመትም ይሁን ከዚያ የረዘመ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ አይንቀሳቀሱም ነበር፤ ደመናው ሲነሣ ግን ጒዞአቸውን ይቀጥሉ ነበር።