ዘፀአት 40:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን የመገናኛው ድንኳን ተተከለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በሁለተኛው ዓመት፣ የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን የማደሪያው ድንኳን ተተከለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ በሁለተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ማደሪያው ተተከለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት በፊተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ድንኳንዋ ተተከለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ በሁለተኛው ዓመት በፊተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማደሪያው ተተከለ። |
እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን በሲና በረሓ ሳሉ፥ እግዚአብሔር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን እንዲህ ሲል አነጋገረው፦
ሙሴ የመገናኛውን ድንኳን ተክሎ በፈጸመበት ቀን ድንኳኑንና የመገልገያ ዕቃዎቹን፥ መሠዊያውንና የመገልገያ ዕቃዎቹን፥ ዘይት በመቀባት ቀደሳቸው፤