ዘፀአት 39:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በደረት ኪሱ ላይ ያሉትን ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ክር አሠሩ፤ በዚህ ዐይነት የደረት ኪሱ ከቀበቶው በላይ ስለሚውል በቀላሉ የማይፈታ ጥብቅ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ተነጥሎ ለብቻው እንዳይንጠለጠል የደረት ኪሱን ቀለበቶች ከመታጠቂያው ጋራ በማገናኘት፣ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋራ በሰማያዊ ፈትል አሰሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው የደረቱ ኪስ በብልሃት ከተጠለፈው ከኤፉዱ ቋድ በላይ እንዲሆን፥ ከኤፉዱም እንዳይለይ የደረቱን ኪስ ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ፈትል አሰሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብሰ እንግድዓው በብልሃት ከተጠለፈው ከመደረቢያው ቋድ በላይ እንዲሆን፥ ከመደረቢያው እንዳይለይ ልብሰ እንግድዓውን ከቀለበቶቹ ጋር ወደ መደረቢያው ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል አሰሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደረቱ ኪስ በብልሃት ከተጠለፈው ከኤፉዱ ቍድ በላይ እንዲሆን፥ ከኤፉዱም እንዳይለይ የደረቱን ኪስ ከቀለበቶቹ ጋር ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል አሰሩት። |
ቀጥሎም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተው በትከሻ ላይ በፊት በኩል ከሚወርዱት ከሁለቱ የኤፉዱ ጥብጣቦች ጋር ከታች በኩል አያያዙአቸው፤ እነርሱም የተያያዙት በብልኀት ከተጠለፈው ቀበቶ በላይ ከመጋጠሚያው አጠገብ ነበር።
የእግዚአብሔር ሞኝነት ነው ተብሎ የሚታሰበው ነገር ከሰው ጥበብ ይበልጣል፤ የእግዚአብሔር ደካማነት ነው ተብሎ የሚታሰበውም ነገር ከሰው ኀይል ይበልጣል።
እግዚአብሔር ጥበበኞችን ለማሳፈር በዓለም እንደ ሞኞች የሚቈጠሩትን ሰዎች መረጠ፤ ብርቱዎችንም ለማሳፈር በዓለም እንደ ደካሞች የሚቈጠሩትን መረጠ፤