ዘፀአት 39:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተው በትከሻ ላይ በፊት በኩል ከሚወርዱት ከሁለቱ የኤፉዱ ጥብጣቦች ጋር ከታች በኩል አያያዙአቸው፤ እነርሱም የተያያዙት በብልኀት ከተጠለፈው ቀበቶ በላይ ከመጋጠሚያው አጠገብ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ልክ ከኤፉዱ መታጠቂያ በላይ፣ ከመጋጠሚያው አጠገብ፣ ከኤፉዱ ፊት ለፊት ካሉት ከትከሻ ንጣዮች ጋራ አያያዟቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፥ በኤፉዱም ፊት፥ ከትከሻዎቹ በታች፥ በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቋድ በላይ፥ በመያዣው አጠገብ አደረጉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፤ በመደረቢያው ፊት፥ ከጫንቃዎች በታች፥ በብልሃት ከተጠለፈ ከመደረቢያው ቋድ በላይ፥ በመያዣው አጠገብ አደረጓቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፥ በኤፉዱም ፊት፥ ከጫንቃዎች በታች፥ በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቍድ በላይ፥ በመያዣው አጠገብ አደረጉአቸው። |
እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በደረት ኪሱ ላይ ያሉትን ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ክር አሠሩ፤ በዚህ ዐይነት የደረት ኪሱ ከቀበቶው በላይ ስለሚውል በቀላሉ የማይፈታ ጥብቅ ነበር።