ዘፀአት 38:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዙሪያ ያለው የአደባባይ አጥርና ወደ አደባባዩ የሚያስገባው ደጃፍ የሚቆሙባቸውን እግሮች፥ እንዲሁም የድንኳኑና በዙሪያው ያለውን የአደባባይ አጥር ካስማዎችን ሁሉ ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአደባባዩ ዙሪያ፣ ለመግቢያው እንዲሁም ለማደሪያው ድንኳን ካስማዎች ሁሉና ለአደባባዩ ዙሪያ ሁሉ እንዲሁ አገልግሎት ላይ አውለውት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩን መግቢያ እግሮች፥ የማደሪያውን ካስማዎች ሁሉና በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን ካስማዎች ሁሉ ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩንም ደጃፍ እግሮች፥ የድንኳኑንም ካስማዎች ሁሉ፥ በአደባባዩ ዙሪያም ያሉትን ካስማዎች ሁሉ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩንም ደጃፍ እግሮች፥ የማደሪያውንም ካስማዎች ሁሉ በአደባባዩ ዙሪያም ያሉትን ካስማዎች ሁሉ አደረገ። |
ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ የሆነው ደጃፍ የሚቆምባቸውን እግሮች፥ ከነሐስ መከላከያው ጋር የነሐስ መሠዊያውን፥ ለመሠዊያው መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ ከዚህ ነሐስ ሠራ፤
ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ ሲያገለግሉ የሚለብሱአቸውን እጅግ የተዋቡትን የካህናት ልብሶች ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ሠሩ፤ የአሮንንም የክህነት ልብሶች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ።