ዘፀአት 38:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አራት የነሐስ እግሮች ባሉአቸው አራት ምሰሶዎች ተደግፎ ነበር፤ ኩላቦቻቸው፥ ጫፎቻቸውና ዘንጎቻቸው ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አራት ምሰሶዎችና አራት መቆሚያዎች ነበሩት፤ ኵላቦቻቸውና ዘንጎቻቸው የብር ሲሆኑ፣ ጫፎቻቸው በብር ተለብጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምሰሶዎቹ አራት ነበሩ፤ ከነሐስ የተሠሩ እግሮች አራት፥ ኩላቦቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ፥ ጉልላቶቻቸውና ዘንጎቻቸው በብር ተለብጠው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከናስ የተሠሩ ምሰሶዎቹም አራት፥ እግሮቹም አራት ነበሩ፤ ኵላቦቹም የብር ነበሩ፤ ጕልላቶቹና ዘንጎቹም በብር ተለብጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከናስ የተሠሩ ምሰሶቹም አራት፥ እግሮቹም አራት ነበሩ፤ ኩላቦቹ የብር ነበሩ፤ ጉልላቶቹና ዘንጎቹም በብር ተለብጠው ነበር። |
ወደ ድንኳኑ የሚያስገባው ደጃፍ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ በፍታ ተፈትሎ በእጅ ጥበብ ካጌጠ ቀጭን ሐር የተሠራ ነበር፤ እርሱም እንደ ድንኳኑ በር መግቢያ መጋረጃዎች ሁሉ ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር ቁመቱም ሁለት ሜትር ነበር፤