ዘፀአት 37:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመክደኛው ላይ አንዱን በአንድ በኩል፥ ሁለተኛውንም በሌላ በኩል አደረገው፤ ከመክደኛውም ጋር አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዱን ኪሩብ በአንዱ ጫፍ ላይ፣ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ጫፍ ላይ ሠራ፤ ከሁለቱ ጫፎች ላይ ከክዳኑ ጋራ አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱን ኪሩብ በዚህኛው በኩል፥ አንዱን ኪሩብ በዚያኛው በኩል አደረጋቸው፥ በሁለቱ ጫፎች ከስርየት መክደኛው ሠራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላ ወገን በዚህና በዚያ ሁለቱን ኪሩቤል ከስርየት መክደኛው በላይ ሠራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርጎ በአንድ ላይ ሠራቸው። |