ዘፀአት 37:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንቡጦቹ ቅርንጫፎቹና መቅረዙ ከተቀጠቀጠ ወርቅ አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ ተሠርተው ከመቅረዙ ጋራ አንድ ወጥ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉብጉቦቹና ቅርንጫፎቹ ከእርሱ ጋር አንድ ነበሩ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተቀረጸ ከጥሩ ወርቅ ተሠርቶ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጕብጕቦችዋና ቅርንጫፎችዋ ከእርሱ ጋር አንድ ነበሩ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተቀረጸ ከጥሩ ወርቅ ተሠርቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕብጕቦቹና ቅርንጫፎቹ ከእርሱ ጋር አንድ ነበሩ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተቀረጸ ከጥሩ ወርቅ ተሠርቶ ነበር። |
“ከንጹሕም ወርቅ መቅረዝ ሥራ፤ የመቅረዙን መሠረትና ዘንግ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፤ ለጌጥ የሚሠሩት የአበባዎች ወርድ እንቡጦችና ቀንበጦች ጨምሮ ከእርሱ ጋር አንድ ሆነው ይሠሩ።
በሩብ ጋሻ መሬት ላይ የተተከለው የወይን ፍሬ ስምንት ሊትር የወይን ጭማቂ ብቻ ይወጣዋል፤ አንድ መቶ ሰማኒያ ኪሎ እህል የተዘራበትም የእርሻ ምርት ዐሥራ ስምንት ኪሎ ብቻ ይገኝበታል።”
ስለዚህ በእናንተ የሚገኙትን የምድራዊ ሕይወት ምኞቶች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም “ዝሙት፥ ርኲሰት፥ ፍትወት፥ ክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማምለክ የሆነ መጐምጀት” ናቸው።