ዘፀአት 36:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእያንዳንዱም መጋረጃ መጠን ተመሳሳይ ሆኖ ርዝመቱ ዐሥራ ሁለት ሜትር፥ የጐኑ ስፋት ሁለት ሜትር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጋረጃዎቹም ሁሉ ተመሳሳይ መጠን ያላቸው ሲሆን፣ ቁመታቸው ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዳቸው አራት ክንድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመቱ ሀያ ስምንት ክንድ፥ ወርዱ አራት ክንድ ነበረ፤ የሁሉም መጋረጃዎች መጠን እኩል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ፤ የመጋረጃዎቹ ሁሉ ልክ ትክክል ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእያንዳንዱ መጋረጃ ርዝመት ሀያ ስምንት ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ፤ የመጋረጆቹ ሁሉ ልክ ትክክል ነበረ። |
ሥራውን ከሚያከናውኑት መካከል እጅግ ጥበበኞች የነበሩት የተቀደሰውን ድንኳን ሠሩ፤ እነርሱም ድንኳኑን ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተሉ፥ የኪሩቤል ሥዕል ከተጠለፈባቸው ዐሥር የበፍታ መጋረጃዎች ሠሩት።