የእያንዳንዳቸው ቁመት አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር የሆነ፥ ከወይራ እንጨት በሁለት ኪሩቤል አምሳል የተቀረጹ ሥዕሎች በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ሠራ።
ዘፀአት 36:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥራውን ከሚያከናውኑት መካከል እጅግ ጥበበኞች የነበሩት የተቀደሰውን ድንኳን ሠሩ፤ እነርሱም ድንኳኑን ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተሉ፥ የኪሩቤል ሥዕል ከተጠለፈባቸው ዐሥር የበፍታ መጋረጃዎች ሠሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሥራ ችሎታ ካላቸው ሰዎች መካከል ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ሁሉ የማደሪያውን ድንኳን በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታና ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ በጥልፍ ዐዋቂ፣ ኪሩቤል ከተጠለፉበት ከዐሥር መጋረጃዎች ሠሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥራ ሲሠሩ ከነበሩት ጥበበኞች የሆኑት ሁሉ ማደሪያውን ሠሩ፤ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ፥ ኪሩቤልም የተጠለፈባቸው ዐሥር መጋረጃዎች ሠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነርሱም ዘንድ ያሉት፥ ሥራ ሲሠሩ የነበሩት በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ ድንኳኑን ከዐሥር መጋረጃዎች ሠሩ፤ እነርሱንም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊም፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ሠሩ፤ በእነርሱም ላይ በጥልፍ ሥራ ኪሩቤልን አደረጉባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነርሱም ዘንድ ያሉት ሥራ ሲሠሩ የነበሩት በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ ማደሪያውን ከአሥር መጋረጆች ሠሩ፤ እነርሱንም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊም ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ሠሩ፤ በእነርሱም ላይ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤልን አደረጉባቸው። |
የእያንዳንዳቸው ቁመት አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር የሆነ፥ ከወይራ እንጨት በሁለት ኪሩቤል አምሳል የተቀረጹ ሥዕሎች በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ሠራ።
ዳዊት የሚኖርባቸውን ቤቶች በራሱ ከተማ በኢየሩሳሌም ሠራ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የሚኖርበትንም ስፍራ አዘጋጅቶ ድንኳን ተከለለት፤
በገባዖን ወደሚገኘው ኰረብታማ የማምለኪያ ስፍራ አብረውት እንዲሄዱ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወደዚያ የሄዱበትም ምክንያት፥ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው፥ እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን በዚያው በገባዖን ስለሚገኝ ነው።
እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤ በመክደኛው ላይ በተሠሩት ክንፍ ባላቸው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ ለእስራኤል ሕዝብ የምታቀርበውን ትእዛዞቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ።
ከእርሱም ጋር እንዲሠራ ከዳን ነገድ የአሒሳማክን ልጅ ኦሆሊአብን መርጬአለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን ነገር ሁሉ እንዲሠሩ ሌሎችም የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ታላቅ ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጌአለሁ።
ወርቁንም ቀጥቅጠው ስስ በማድረግ እንደ ክር አድርገው ቈራረጡት፤ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለም ጥሩ በፍታ ጋር በጥበብ አሠራር ጠለፉት።