ዘፀአት 34:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሙሴ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ልክ እንደ ፊተኞቹ ቀረጸ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ጽላቶቹን ይዞ ወደ ሲና ተራራ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሙሴ እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላት ጠርቦ፣ እግዚአብሔር እንዳዘዘው በማለዳ ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ ሁለቱን የድንጋይ ጽላትም በእጆቹ ያዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንደ ፊተኞቹ አድርጐ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጠረበ፤ በማግስቱም ማልዶ ጌታ እንዳዘዘው ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች በእጁ ይዞ ወደ ሲና ተራራ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እንደ ፊተኞቹ አድርጎ ሁለት የድንጋይ ጽላት ቀረጸ፤ ሁለቱንም የድንጋይ ጽላት በእጁ ወሰደ፤ በነጋውም ማልዶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እንደ ፊተኞቹ አድርጐ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረበ፤ በነጋውም ማልዶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ፥ ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች በእጁ ወሰደ፥ |
ሙሴም ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደ ተራራው ወጣ፤ እግዚአብሔርም ከተራራው ላይ በመናገር የያዕቆብ ተወላጆች ለሆኑት እስራኤላውያን እንዲህ ብሎ እንዲናገር አዘዘው፥
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመጀመሪያዎቹን የሚመስሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ቅረጽ፤ እኔም አንተ በሰበርካቸው ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ቀድሞ የተሰበሩትን የድንጋይ ጽላቶች አስመስለህ በምትካቸው ሁለት ጽላቶች ቅረጽ፤ ለእነርሱ ማኖሪያ የሚሆን ታቦትም ከእንጨት ሥራ፤ እኔም ወዳለሁበት ተራራ ውጣ፤
“ስለዚህም እኔ ከግራር እንጨት ታቦትን ሠራሁ፤ እንደ ፊተኞቹ ያሉትንም የድንጋይ ጽላቶች በመቅረጽ አዘጋጀሁ፤ እነርሱንም በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ፤