ዘፀአት 32:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮን ሕዝቡን በጠላቶቻቸው ፊት መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ መረን እንደ ለቀቃቸው ሙሴ ተመለከተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ከቍጥጥር ውጭ እንደ ሆኑ፣ አሮንም መረን እንደ ለቀቃቸውና በጠላቶቻቸውም ዘንድ መሣለቂያ እንደ ሆኑ ሙሴ አስተዋለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴ በጠላቶቻቸው ፊት መሳለቂያ እንዲሆኑ አሮን ስድ ለቅቋቸዋልና ሕዝቡ ስድ እንደ ተለቀቁ ባየ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በጠላቶቻቸው ፊት እንዲነወሩ አሮን ስድ ለቅቆአቸዋልና ሕዝቡ ስድ እንደ ተለቀቀ በአየ ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በጠላቶቻቸው ፊት እንዲነወሩ አሮን ስድ ለቅቍቸዋልና ሕዝቡ ስድ እንደ ተለቀቁ ባየ ጊዜ፥ |
በዚህም ጉዳይ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆችን ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ “ከዚህ በፊት ታደርጉት በነበረው ዐይነት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ ይበቃችኋል፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው!” አለ።
የይሁዳ ንጉሥ አካዝ በሀገሩ ላይ ክፉ ነገርን ስላስፋፋና ለእግዚአብሔር የነበረውን ታማኝነት ስላጐደለ፥ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ችግርና መከራ እንዲወርድ ፈቀደ።
ስለዚህ በሰፈሩ ደጃፍ ቆሞ “የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ!” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ፤ ሌዋውያንም ሁሉ በዙሪያው ተሰበሰቡ፤
እንግዲህ በሥልጣን ላይ ወዳሉት ገዢዎች ሄጄ፥ ከእነርሱ ጋር እነጋገራለሁ፤ በእርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉ፤” ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀዋል፤ ለእርሱም መታዘዝ እምቢ ብለዋል።
ይህንንም የማደርገው፥ ለፈጸምሽው በደል ሁሉ ይቅርታ ሳደርግልሽ ሥራሽን በማስታወስ በድንጋጤ ዐፍረሽ ጸጥ እንድትዪ ነው፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።
ሞተው ዐፈር የበላቸው ሁሉ ይነሣሉ፤ ከእነርሱም ከፊሎቹ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሲገቡ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት ይላካሉ።
እናንተ የሻፊር ሕዝቦች ራቊታችሁን ምርኮኞች ሆናችሁ በዕፍረት ዕለፉ፤ የጻእናን ኗሪዎች ከከተማው ለመውጣት አይደፍሩም፤ ቤትኤጼል ራስዋ የለቅሶ ቦታ ስለ ሆነች ለእናንተ መጠጊያ ልትሆን አትችልም።
“እነሆ! እኔ እንደ ሌባ በድንገት እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይሆንና ኀፍረቱን ሰዎች እንዳያዩበት ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው የተመሰገነ ነው!”