ዘፀአት 32:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ወደ ሰፈሩ ተጠግቶ ጥጃውንና ጭፈራ ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ ይዞአቸው የመጣውንም ጽላቶች በተራራው ሥር ወርውሮ ሰባበራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ወደ ሰፈሩ ደርሶ ጥጃውንና ጭፈራውን ባየ ጊዜ ቍጣው ነደደ፤ ጽላቱን ከእጁ በመወርወር ከተራራው ግርጌ ሰባበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ ጥጃውንና ዘፈኑን አየ፤ የሙሴ ቁጣ ነደደ፥ ጽላቶቹን ከእጁ ወርውሮ ከተራራው በታች ሰበራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ ጥጃውንም ዘፈኑንም አየ፤ የሙሴም ቍጣ ተቃጠለ፤ እነዚያንም ሁለቱን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተራራው በታች ሰበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ ጥጃውንም ዘፈኑንም አየ፤ የሙሴም ቁጣ ተቃጠለ፥ ጽላቶቹንም ከእጁ ጥሎ ከተራራው በታች ሰበራቸው። |
ሙሴ ግን እግዚአብሔር አምላኩን በመማለድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ በሥልጣንህና በታላቅ ኀይልህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸውን ሕዝብህን እስከዚህ የምትቈጣው ስለምነው?
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመጀመሪያዎቹን የሚመስሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ቅረጽ፤ እኔም አንተ በሰበርካቸው ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ።
ይህም ቃል ኪዳን እነርሱን ከግብጽ ለማውጣት እጃቸውን በያዝኩ ጊዜ እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እኔ አምላካቸው ብሆንም እንኳ እነርሱ ቃል ኪዳኔን አልጠበቁም፤ እኔም ችላ አልኳቸው፤
ከዚህ በኋላ “አንድነት” የተባለውን ሁለተኛውን በትር ሰበርኩት፤ ይህንንም ማድረጌ በይሁዳና በእስራኤል መካከል የነበረው ወንድማማችነት መጥፋቱን ለማመልከት ነበር።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቈጣ ሁሉ ይፈረድበታል፤ ደግሞም ወንድሙን፥ ‘አንተ የማትረባ!’ ብሎ የሚሳደብ በሸንጎ ይፈረድበታል፤ ‘ደደብ!’ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ በገሃነመ እሳት ይፈረድበታል።
ኢየሱስም ይህን በማየት ተቈጥቶ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፤ ተዉ፤ አትከልክሉአቸው፤
ኢየሱስም ስለ ልባቸው ድንዛዜ አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በቊጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት።
“ሰዎች ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ከመጠን በላይ ሊፈነጥዙ ተነሡ” ተብሎ ስለ እነርሱ እንደ ተጻፈው፥ እነርሱ ጣዖትን እንዳመለኩ እናንተም እንደእነርሱ ጣዖትን አታምልኩ።